#ETH

#ETH


አፍሪፖል

እ.ኤ.አ በመጋቢት ወር 2019 ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ ናይሮቢ በረራዉን ሲያደርግ በነበረዉ ET 302 የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዉሮፕላን ቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ በመከስከሱ የ35 ሀገራት መንገደኞች ህይወት ማለፉ ይታወሳል፡፡ አደጋዉ ከደረሰ ከሁለት ቀናት በኃላ ኢትዮጵያ በጠየቀችዉ ጥያቄ መሰረት ኢንተርፖል ምላሽ ሰጪ ቡድን በመላክ ምርመራዉን ሲያከናዉን ቆይቷል፡፡ ለህልፈተ ህይወት የተዳረጉትን ለመለየት እንዲረዳዉም ኢንተርፖል የተጎጂ ቤተሰቦች ዲ ኤን ኤ በማሰባሰብ ምርመራ አድርጓል፡፡ ኢንተርፖል ለአደጋዉ ምላሽ ሰጪ ቡድን በማሰማራት ስሰራ የነበረዉን ተጎጂዎችን የመለየት ስራ ከ 6 ወራት በኃላ በተሳካ ሁነታ ማጠናቀቅ መቻሉን አፍሪፖል በድህረ ገፁ ባወጣዉ መረጃ አስነብቧል፡፡ ምላሽ ሰጪ ቡድኑ በአለም አቀፍ ደረጃ የሞት አደጋ የደረሰባቸዉን የሚለዩ ህግ አስፈፃሚዎችን በማስተባበር እና በአባል ሀገራት የቀረበዉን የቅድመ ሞት መረጃን የማቀናጀት ሚና ተጫዉቷል ተብሏል፡፡ ቡድኑ የሞት አደጋ የደረሰባቸዉን የመለየት ምርመራዉ ዓለም አቀፋዊ ደረጃዉን ጠብቆ መካሄዱን ለማረጋገጥ እንዲሁም የጣት አሻራ እና የ ዲ ኤን ኤ ናሙናዎችን በማሰባሰብ እገዛ ማድረጉም ተገልጿል፡፡በአዲስ አበባ የሚገኘዉ የኢንተርፖል ልዩ ተወካይ ፅፈት ቤትም ለህልፈተ ህይወት የተዳረጉትን የመለየት ስራን በማስተባበር ድጋፍ ማድረጉ ተገልጿል፡፡ ከ14 የአፍርካ ሀገራት የተዉጣጡ መቶ የሚደርሱ ባለሙያዎች እንዲሁም የአሜሪካ እና የአዉሮፓ ሀገራት ባለሙያዎች ባካሄዱት ምርመራ 48 የሚደርሱ ሟቾችን በጣት አሻራዎቻቸዉ መለየት ችለዋል ተብሏል፡፡

Via Ethiopian Federal Police

Report Page