#ETH

#ETH


አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በ2016 እ.አ በሪዮ ኦሎምፒክ ያገኘውን ሜዳሊያ በኢትዮጵያ ለውጥ ለማምጣት ለተሰዉ ሰማዓታት መታሰቢያነት እሰጣለሁ ባለው መሰረት ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ የርክክብ ስነ ስርዓት ተካሒዷል፡፡

አትሌቱ በገባው ቃል መሰረት በሪዮ ኦሎምፒክ ያገኘውን ሜዳሊያውን ለኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ አስረክበዋል፡፡

ሜዳሊያው አትሌት ታሪኩ በቀለና እጅጋየሁ ዲባባ ለፕሬዝዳንቱ አስረክበዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ታሪካዊ በሆነው ሜዳሊያ ርክክብ መድረክ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር አትሌት ፈይሳ ችግራችንን በአለም አቀፍ ህ/ብ ዘንድ ለማድረስ የታገለ ጀግና ነው ብለዋል፡፡

በትግሉ ለተሰዉ ቄሮዎችና ቀሬዎች መታሰቢ ሀውልት እንደሚቆም በመድረኩ ቃል ገብተዋል፡፡

በተጨማሪም የተረከቡት ሜዳሊያና ሌሎች መታሰቢያዎች፣ ጥናት የሚከናወንበት ማዕከል እንደሚገነባም ተናግረዋል፡፡

የኦሮሞ ህዝብ የተገኙ ድሎች ወደ ኃላ የማይቀለበስበት ደረጃ ለማድረስ ቀን ከሌሊት መስራት አለበትም ነው ያሉት፡፡

በአትሌቱ ለሚቋቋመው ፋውንዴሽን የክልሉ መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል፡፡

ሁሉም በመደማመጥ ና አንተ ትብስ አንተ በመባባል የአስተዳደር ችግርን ለመፋታት እጅ ለእጅ ተያይዘን መስራት ይጠበቅብናልም ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በበኩላቸው በኦሎምፒክ ሜዳ ላይ ሌሎች ደስታቸውን ሲገልፁ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ የኢትዮጵያን ህዝብ ችግር ና ሀዘን ሲገልጽ ቆይቷል ብለዋል ፡፡

አትሌቱ በአለም አቀፍ ማህ/ብ ዘንድ ድምፃችን እንዲሰማ አድርጓል ያሉት ኢንጂነር ታከለ በዚህም ትግሉ በመፋፋም በሀገሪቱ ለውጥ መጥተዋል ብለዋል፡፡

በዚህም አትሌት ፈይሳን ብናመሰግነው ቢያንስበት እንጂ አይበዛበትም ብለዋል፡፡

Via OBN

Report Page