#ETH

#ETH


"ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ!" በሚል መሪ ሀሳብ 18 ዓመታትን በስኬት የተጓዘው ታላቁ ሩጫ በቅርቡ አለማቀፍ እውቅና ማግኘቱ የሚታወስ ሲሆን ዘንድሮም ህዳር 7 "ሴቶች ልጆች በእኩል ሚዛን መታየት መደመጥ እና ተቀባይነት ሊኖራቸው ይገባል" በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል፡፡ በዚህ ታላቅ ሩጫ የሚገኘው ገቢ በተለያዩ አከባቢዎች ላሉ ማህበረሰቦች ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት እንደሚውል አዘጋጆቹ ያስታወቁ ሲሆን በእንግድነት የተገኙት የትምህርት ሚኒስትር ሚኒስተር ዴኤታ ወ/ሮ ጽዮን ተክሉ ታላቁ ሩጫ ሊገነባው ላሰበው ትምህርት ቤቶች ምስጋናቸውን አቅርበው የዘንድሮ መሪ ቃሉን ለአንድ ቀን ብቻ ሳይሆን አመቱን በሙሉ በልባችን ይዘን መንቀሳቀስ ይጠበቅብናል የሚል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በዛሬው መርኃግብር ላይ ይፋ እንደተደረገው በዘንድሮው ሩጫ 1.9 ሚሊዮን ብር ለበጎ አድራጎት ስራ ለመሰብሰብ መታቀዱንና ሁሉም ሰው ለበጎ አድራጎት የሚውለውን ቲሸርት ከማንኛውም ዳሽን ባንክ ቅርንጫፍ አሊያም በአሞሌ መግዛት ይቻላል ተብሏል፡፡ የዘንድሮው ትምህርት ቤቶችን ማስገንባት ዓላማ የተቀረጸው በሻለቃ ሀይሌ ገ/ሥላሴ ተነሳሽነት የተገነባው ትምህርት ቤት አስመልክቶ ይህንን ተግባር ወደፊት ለማስቀጠል ታስቦ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በፕሮግራሙ ላይም ይህንን ስራ የሚያሳይ አጭር ፊልም ቀርቧል፡፡ ቲሸርቱንም ከጥቅምት 28-30 ድረስ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በታላቁ ሩጫ የስፖርት ኤክስፖ ላይ ይሰጣል፡፡ አዘጋጆቹ አክለውም ከሩጫው አንድ ቀን አስቀድሞ 3,500 ልጆች የሚሳተፉበት የህጻናት ውድድር የሚካሄድ ይሆናል ብለዋል፡፡

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia


Report Page