#ETH

#ETH


ሀዋሳ ከተማ በመጪው ጥቅምት ወር የባለኮከብ ሆቴሎች መድረክን ታስተናግዳለች!

የሀዋሳ ከተማ ሙሉ ለሙሉ ወደቀደመው ሰላምና መረጋጋቷ መመለሷንና በአሁኑ ወቅት ያለምንም ስጋት የሚሰሩባትና የሚንቀሳቀሱባት ከተማ መሆኗን አዲሱ የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ገለፁ። በመጪው ጥቅምት መጀመሪያ ከ700 በላይ ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት የባለ ኮከብ ሆቴሎች መድረክን እንደምታስተናግድም ገልፀዋል።

ምክትል ከንቲባው አቶ ጥራቱ በየነ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳስታወቁት፤ ከተማዋ ባለፈው ሀምሌ ከሲዳማ ዞን ክልል የመሆን ጥያቄ ጋር በተያያዘ ተፈጥሮ ከነበረው የሰላምና መረጋጋት እጦት ተላቃለች። በከተማዋ የሚገኘው የኮማንድ ፓስት፣የክልሉ የጸጥታ ሃይልና ህዝብ በጋራ ባከናወኑት ተግባር በአሁኑ ወቅት የነዋሪው ፣የንግዱ ማህበረሰብ እና የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ወደ ቀድሞው ሁኔታ ተመልሷል።

‹‹ሀዋሳ አሁን ያለምንም ስጋት የሚሰሩባትና የሚንቀሳቀሱባት ከተማ ሆናለች›› ያሉት ምክትል ከንቲባው፣ ባለሀብቶችና የንግዱ ማህበረሰብ ወደ ከተማዋ መጥተው እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል። ቱሪስቶችም ሆኑ ለተለያዩ ስራዎች ወደ ከተማዋ መምጣት የሚፈልጉ ሁሉ ያለምንም ስጋት ወደ ከተማዋ መምጣት እንደሚችሉም ጠቁመዋል። በተለይ ኢንቨስት ለማድረግ የሚመጡ አካላትን ከተማ አስተዳደሩ ከመቼውም ጊዜ በተሻለ ለማገልገል ዝግጁ መሆኑንም አረጋግጠዋል።

Via #EPA

@tsegabwolde @tikvahethiopia


Report Page