#ETH

#ETH


“ ለ14 ዓመታት ያህል ኦነግ ነው ብሎ አቶ ጌታቸው አሰፋ ይከታተለኝ ነበር፤ እርሱ የኦሮሞ ብሔርን ማየት አይፈልግም፤ ኦሮሞ ከሆንክ አንተ ለእርሱ ኦነግ ነህ ማለት ነው ” አቶ ጁነዲን ሳዶ

*

*

*

አቶ ጁነዲን ሳዶ ከአዲስ ዘመን ጋር ካደረጉት ቃለምልልስ መካከል የተወሰዱ ጥቂት ነጥቦች

• ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በነበሩበት ጊዜ ምንም የማያወላዳ የህወሃት የበላይነት አለ። ይህ በፖሊሲ ደረጃ ነው።

• በምርጫ 97 የኢህአዴግ ደረት ትንሽ አበጥ ያለበት ሁኔታ ነበርና ለተቃዋሚዎች ትኩረት አልተሰጠም።

• ከሃይማኖት ጋር ተያይዞ የሚነሱብኝ ጉዳዮች የፖለቲካ ሥራ ነው የተሰራባቸው። የፖለቲካ ሥራውን የሰሩት ሰዎች ደግሞ ከፌዴራል መንግሥቱ ውስጥ ከኢህአዴግም ከኦህዴድም ውስጥ ናቸው።

• የደህንነት መስሪያ ቤቱ ነበር የተሳሳቱ መረጃዎችን በሕዝቡ መካከል ሲያሰራጭ የነበረው። በግል ከአቶ ጌታቸው አሰፋ ጋር አንስማማም።

• አሃበሽ የሚባል ባዕድ ሃይማኖት እንዲገባ ያደረገው እሱ ነው ይላሉ።

• መስኪድ አሰራ ስለሚባለው እኔ በሕይወቴ እስከአሁን ያሰራሁት አንድ መስኪድ ብቻ ነው። እናቴ ስታርፍ አርሲ የተወለድኩበት ቦታ ላይ በአርሲ ባህል «በጌጌሳ» ገንዘብ አሰባስቤ ነው የሰራሁት፤ በልመና።

• ለ14 ዓመታት ያህል ኦነግ ነው ብሎ አቶ ጌታቸው አሰፋ ይከታተለኝ ነበር። እርሱ የኦሮሞ ብሔርን ማየት አይፈልግም ኦሮሞ ከሆንክ አንተ ኦነግ ነህ ማለት ነው ለእርሱ።

• ኦነጎች በበኩላቸው መንግሥት ውስጥ በመሆኔ የሚቀሰቅስብን እና የሚያስቸግረን እሱ ነው ብለው እኔን የሚጠሉበት ሁኔታ አለ። ይሁንና አቶ ጌታቸው አሰፋ ኦነግ ነው ብሎ ፋይል ከፍቶብኝ ስልኬን እያስጠለፈ በርካታ ችግር አድርሶብኛል።

• እኔን ምክንያት አድርገው ባለቤቴን ስላሰሯት ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ ገብቼ ነበር። የመጨረሻው ልጄ ከእናቱ ተለይቶ የማያውቅ ገና የአራት ዓመት ሕፃን ነበር። ባለቤቴን ፍቷትና እኔን እሰሩኝ ብል ማንም ሊሰማኝ አልቻለም።

• ለህክምና ታይላንድ ነው በቀጥታ የሄድኩት። ታይላንድ ለአንድ ወር በህክምና ቆየሁና ወደዱባይ አመራሁ። ዱባይ ሁለት ወር ቆይቻለሁ። እዚያ ተራ ሥራ እየሰራሁ ኑሮን ለመግፋት አስቤ ነበር ግን አልሆነም።

• በኬንያ 12 ወር ቆይቻለሁ። በወቅቱ ትንሽ ከተማ ውስጥ ተደብቄ ነበር። ኬንያ ውስጥ ብዙ ኢትዮጵያውያን ተገድለዋል። ታስረው መጥተውም ደብዛቸው የጠፉ አሉ። እኔ የት እንዳለሁ አቶ ጌታቸው አሰፋ ቢያውቅ ስለሚያስረኝ የምጠቀመው ስልክ እንኳን ኢንተርኔት የሌለው ነበር።

• በኋላ ከኬንያ ወደአሜሪካ አቀናሁ። እናም እንኳን የደህንነት ሰዎች ሊደግፉኝ ቀርቶ ሲያሳድዱኝ የነበሩት እነሱ ነበሩ።

• አሜሪካ ስገባ ይህ ሁሉ የደረሰብኝ ለበጎ ነው በማለት እራሴን ወደሃይማኖቴ በመመለስ እንደገና ውስጤን ለማየት ቻልኩ፡፡ ለሰዎችም ይቅርታ ማድረግ ጀመርኩ።

• አሁን ጌታቸው አሰፋን ባገኘው ቀድሞ እንደምናደድበት አልናደድበትም፡፡ ይልቁንም ሰላም እለዋለሁ። እርሱም አሁን ችግር ውስጥ ነው።

• ከለውጡ በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ እና አቶ ለማ መገርሳ አሜሪካ በሄዱበት ወቅት አግኝቻቸዋለሁ። ሀገሬ መመለስ እፈልጋለሁ ስላቸው ዶክተር ዐብይ ዝግጁ ከሆንክ አሁኑኑ እንድትመጣ ነበር ያለኝ።

• አሁን ገንዘብ ስለሌለኝ አቅም ካላቸው ሰዎች ጋር እየተባበርኩ ለመስራት ነው ሃሳቤ። ባለሀብቶችን ማሰባሰብ እና ማሳመን የሚጠይቅ ሥራ ላይ ተሰማርቻለሁ።

• ለውጥ በሚኖርበት ጊዜ ግጭቶች ይጠበቃሉ። ግጭት ባይኖር ነበር ጤነኛ የማይሆነው። እዚህም እዚያም የሚፈነዳዱ ነገሮች በአግባቡ ከተያዙ ወደትክክለኛ መፍትሄ ይመጣሉ። ዋናው ነገር መንግሥት ጠንካራ መሆን መቻል አለበት።

• ጠንካራ የሚሊተሪ አቅም ወይም የፖሊስ አቅም ብቻ ሳይሆን የመንግሥት ጥንካሬ በንግግር ቃላት፣ በተግባር ማሳየት፣ በመዋቅር እና በፍትህ ይገለጻል።

• መንግሥት የሚችለውን እሰራለሁ የማይችለውን አልችልም ማለት አለበት። የሃሰት ቃል እየተገባ ከሄደ የሕዝብ አመኔታ እና አክብሮቱ ይታጣል።

• መንግሥት ቆፍጣና ሆኖ የእራሱን ሰዎች በአግባቡ ማሰማራት ካልቻለ ሕዝቡ አያከብረውም። ከዚህ ባለፈ ግን እንደ አጠቃላይ ሕግ የበላይነት ላይ ማወላዳት አያስፈልግም።

• ኢትዮጵያም ሙሉ የምትሆነው ከብሔር ብሔረሰቦቿ ጋር ነው። አንዱን በኢኮኖሚም ሆነ በማህበራዊ ጉዳይ አግልሎ ሌላው ሊያድግ አይችልም። በዚህ ረገድ አንዱ ለአንዱ ስጋት መሆን የለበትም።

• ሜቴክ ገንዘብ ስለዘረፈ የትግራይ ሕዝብ አብሮ መጨፍለቅ የለበትም የሚል አስተሳሰብ ይዘን መጓዘ ያስፈልጋል፡፡

• ጥቂት የኦዲፒ ባለሥልጣናት ካጠፉ ኦሮሞ ሕዝብን በአንድ ላይ መፈረጅ ኢትዮጵያዊነትን ያላላል። እናም ሁሉም አካታችነትን ሳይለቅ ሁሉም ተከባብሮ ሲኖር ነው ጥንካሬ የምናገኘው።

• ክልል መሆን ኢማዕከላዊነትን አያሳይም። ወደፊት እኮ ክልሎችም መልሰው ሊዋሃዱ /Re union/ ሊደረግ ይችላል።

Via EPA

Report Page