#ETH

#ETH


"27 ዓመት ጨለማ ነበረ፣ የጥፋት ዘመን ነበረ፤ ውሸት። በ27 ዓመት ውስጥ በአገሪቱ ውስጥ ለተፈጠሩ ጥፋቶች በሙሉ ተጠያቂው ህወሓት ነው፤ ውሸት። ባለፉት 27 ዓመታት ውስጥ ኢህአዴግ በአገሪቱ ያስመዘገባቸው ድሎች quantitatively & qualitatively የታወቁ ናቸው። እኔ አሁን ይሄ ይሄ ብየ አልዘረዝርም፤ የሚታወቅ ስለሆነ። ግን ለምሳሌ ኢህአዴግ አገሪትዋ ሲረከብ (per capital income) ወደ 90 ዶላር አከባቢ ነበረ፤ ወደ 800 ዶላር ማድረስ ተችለዋል። የትምህርት ቤት፣ መንገድ ወዘተ ማስፋፋትም እንደዚሁ። በሰላም፣ በህዝበች መፋቀር የተመዘገበው ድል ወዘተ የሚታወቅ ነው። በአጠቃላይ ኢህአዴግ የሰራው ስራ አገሪትዋ ከነበረችበት ደረጃ በማነፃፀር ከለካነው ያስመዘገበው ድል A+ A+ A+ ነው። ከጎረቤት አገሮች ከተወዳደርንም እንደዚሁ የተመዘገበው ድል ተአምር ነው። ከራሳችን አላማ፣ መስራት ከምንፈልገው ሲወዳደር ግን ትንሽ ነው። ምናልባት B- ወይም C ላይ ነን።

በአገሪቱ ለተከሰቱ ችግሮች ተጠያቂው ማን ነው? ለሚለውም በተሃድሰው ጊዜ ተጠያቂው ማን እንደሆነ በግልፅ ለይተን አስቀምጠናል። ህወሓት በተሃድሰው የ35 ቀናት በወሰደው የግምገማ መድረክ ላይ ራሳዋን በሚገባ አይታለች። በአገሪቱ ውስጥ ለነበራት ድርሻም በሚገባ ወስዳለች። ተጠያቂው እንትና ነው፣ ምናምን ብላ Externalize አላደረገችም። የግምገማው ይዘት ወደ ኢህአዴግ ሲቀርብም ህወሓት አብዝተዋለች ነው የተባለው። ያኔ ህወሓት ነች ተጠያቂ አልተባለም። ተጠያቂው የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር ነው፤ ተብሎ ነው የተቀመጠው። በተለይ ሊቀ መንበሩና ምክትል ሊቀ መንበሩ (ጠቅላይ ሚኒስትሩና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ) ደግሞ የበለጠ ተጠያቂዎች ናቸው ተብሎ ተገምግመዋል። እና 27 ዓመት ጨለማ ነበረ፣ የጥፋት ዘመን ነበረ፤ በ27 ዓመት ውስጥ በአገሪቱ ውስጥ ለተፈጠሩ ጥፋቶች በሙሉ ተጠያቂው ህወሓት ነው፤ የሚለው ነገር ውሸት ነው"።

ታጋይ አቦይ ስብሃት ነጋ

ከአውሎ ሚድያ ካደረገው ቆይታ የተወሰደ

Report Page