#ETH

#ETH


በኢትዮጲያ የጦማሪያን ማህበር ቢቋቋም ጠቀሜታው ምን ይሆን?

በዩኔስኮ አዘጋጅነት ሲካሄድ የነበረው የጦማሪያን ፎረም ማምሻውን ተጠናቋል፡፡ ፎረሙ ከደቡብ አፍሪካ፣ ከኡጋንዳና ከኬኒያ የመጡ እንግዶች ያላቸውን ልምድም ያካፈሉበት መድረክ ሆኖ አልፏል፡፡ በተለይ በኬኒያ ያለው የጦማሪያን ማህበር በኢትዮጵያ ማህበሩ ቢቋቋም ከተጠያቂነት፣ መብትን ከማስከበር፣ ሀገራዊ ጉዳዮችን እንደ ዓላማ ይዞ ከመንቀሳቀስና በኬኒያ ካጋጠማቸው የመንግስት ጫና ጋር በማጣቀስ ለተሳታፊዎች ልምዳቸውን አካፍለዋል፡፡


በከሰዓቱ መርኃግብር ከተነሱ ኃሳቦች መካከል አንዱ በኢትዮጵያ የጦማሪያን ማህበር ሟቋቋም የስፈልጋል ወይ? የሚል ምክረ-ሀሳብ በዞን ዘጠኝ ጡምራ መድረክ ላይ ሲሳተፉ በነበሩት በአቤል ዋብላ እና በፍቃዱ ኃይሉ ቀርቦ በተሳታፊው ውይይት ተደርጎበታል፡፡ እንደ አቅራቢዎቹ ገለጻ በሀገራችን የጡመራ ሥራ በሦስት ዘመን ከፍለው አሳይተዋል፡፡ በ1997 ምርጫ ወቅት ጦማሪያን በስፋት የነበሩበት ጌዜ እንደ ነበርና ከዛ በኀላ ባሉት አመታት ከስርዓቱ ጋር ተያይዞ በጣም የቀዘቀዘበትና የሀሳብ ነጻነት የተገደበበት ጊዜ እንደነበር ገልፀዋል፡፡ ሦስተኛው የጡምራ ዘመን ተብሎ የተጠቀሰው የአሁኑ የሶሻል ሚዲያው እንቅስቃሴ ሲሆን ብዙ ሀሰተኛ መረጃዎች የሚንሸራሸሩበትና ትንተናው በስሜታዊነት፣ ሌሎች ተሞክሮዎችንና የመፍትሔ ሀሳቦችን የሚጠቁም ባለመሆኑ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ይገኛል በማለት ገልፀዋል፡፡


ሀሳቡ ወደ ተሳታፊዎች ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ተሳታፊዎችም በመጀመሪያ ጦማሪ (Blogger) የሚለው ስም በራሱ ሰፉ ብሎ ሌሎችን ማህበራዊ ድረ-ገጾች ባካተተ መልኩ መታየት ያለበትና ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራ መሰራት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ ከዛም በተጨማሪ ወጥ የሆነ፣ ሁሉንም ሀሳብ የሚያስተናግድ ፣ አቃፊ፣ በሁሉም አከባቢ የሚገኙና በተለያዩ የሙያ መስኮች የተሰማሩ ግለሰቦች የሚቀላቀሉበት እንዲሆን ሀሳብ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በአሁኑ ወቅት ጦማሪያን የፓለቲካ ጉዳዮችን ብቻ የሚያነሱ ሆነው መታየት የለባቸውም ያሉት ተሳታፊዎቹ በሁሉም መስክ መስፋት ያለበትና በተለያዩ ሞያ ውስጥም ያሉ አካላት በሞያቸው ቢሳተፉ ያለውን መልካም አስተዋፅኦ አንስተዋል፡፡ 

በተለይ በማህበር መደራጀታቸው ደግሞ ከመንግስትም ሆነ ከሌላ አካል በሙያው ላይ የሚደርሱትን ጫናዎች ለመቋቋም ከፍተኛ ጥቅም እንዳለው ተጠቁሟል፡፡ በቀጣይም ይህንን ማህበር ከመመስረት አኳያ መነሻ ሥራዎችን የሚሰሩ ፈቃደኛ ቡድን የተቋቋመ ሲሆን ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

#TikvahEthiopia

Report Page