#ETH

#ETH


በ2011ዓ.ም ሁሉንም አይነት አደገኛ እጾችን በቁጥጥር ስር ማዋሉንና ከወንጀል ድርጊቱ ጋር በተያያዘ ተሳታፊ የሆኑ 80 ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ፌዴራል ፖሊስ ገለጸ። በአዲስ አበባ ከተማ ለመልሶ ማልማት በተከለሉና በሻሸመኔ አካባቢ የተተከሉ እፆችን እንዲወገድ ማድረጉንም ጠቁሟል።

በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ዘርፍ የአደገኛ ዕጽ ቁጥጥር ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር መንግስተአብ በየነ በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለጹት፤ ባለፈው ዓመት ከሐምሌ አንድ ቀን 2010 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ሁሉንም አይነት አደገኛ እጽ በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል።

ኮኬይን 186 ኪሎ ግራም፣ ሄሮይን ዘጠኝ ነጥብ ሁለት ኪሎ ግራም፣ ካናቢስ አንድ ሺ አንድ መቶ አራት ኪሎ ግራም በቁጥጥር ስር ማዋሉንና ከወንጀል ድርጊቱ ጋር በተያያዘ 80 ሰዎችን በቁጥጥር ሰር ማዋሉን ተናግረዋል። የወንጀል ድርጊቱ ተሳታፊዎቹ የ17 የተለያዩ አገራት ዜግነት ያላቸው ሲሆኑ፤ 57 ወንዶች እና 23 ሴቶች መሆናቸውንም አክለው ገልፀዋል።

በአዲስ አበባ ከተማም ፈርሰው ለመልሶ ግንባታ እና ለልማት ታጥረው በቆዩ ቦታዎች ግንባታቸው ባለመከናወኑ እንዲሁም እንደመደበቂያም ስለሚጠቀሙባቸው በእነዚህ ቦታዎች የአደገኛ ዕጽ ብቅለቱ አልፎ አልፎ እንደሚታይ ኮማንደር መንግስተአብ ተናግረዋል። ‹‹አደገኛ ዕጽ ብቅለት በተጨባጭ እየደረስንበት እያስወገድን እንገኛለን። አሁን በክረምቱ ወራት እንኳን ቂርቆስ፣ ኮልፌ እና ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች ሁለት ሶስት ጊዜ አጋጥሞን በተደጋጋሚ አስወግደናል›› ብለዋል።

Report Page