#ETH

#ETH


ባዕድ ነገር በመቀላቀል እንጀራ እያጋገሩ ለገበያ ያቀርባሉ ያላቸውን ሁለት ግለሰቦች በህዝብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን የን/ስ/ላ/ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አሰታወቀ፡፡

ፖሊስ መምሪያ ከህዝብ የደረሰውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ መስከረም 13 ቀን 2012 ዓ.ም በወረዳ 3 ክልል መካኒሳ አቦ ጀርባ በተከራዩት ቤት ውስጥ ባዕድ ነገር በመቀላቀል እንጀራ እየጋገሩ ለገበያ ያቀርባሉ ያላቸውን ሁለት ግለሰቦችን መያዙን አስተውቋል፡፡

በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ የመካኒሳ አከባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል መርማር ረ/ሳጅን ስሜነህ ብድሬ እንደሳወቁት ፖሊስ ከህዝብ የመጣውን ጥቆማ ለወረዳ ንግድና እንዱስትሪ ዕ/ቤት እና ለምግብ መድሃኒትና ጤና እክብካቤ አስተዳደር ዕ/ቤት በመሳወቅ በቦታው ተገኝተው ሁኔታውን በጋራ ማጣራታቸውን አስታውቀዋል፡፡

እንጀራው በሚጋገርበት ቤት ውስጥ በ8 ቤርሚል የተቦካ ሊጥና ዱቄት መገኘቱን የገለጹት ረ/ሳጅን ስሜነህ የዱቄቱ ናሙና ለሚመለከተው አካል ተልኮ ስለምያስከተለው ጉዳት ለማረጋገጥ ምርመራ እንደሚደረግ እና ከጉዳዩ ጋር በተያያዘም ሁለት ተጠርጣርዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተናግረዋል፡፡

የወረዳ 3 የምግብ መዳሃኒትና የጤና እንክብካቤ አስተዳደር ዕ/ቤት ኃላፊ አቶ አሰፋ በላይ በባኩላቸው ተጠርጣርዎቹ እንጀራውን እየጋገሩ ለገበያ የሚያቀርቡት ከዕ/ቤቱ የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫና የንግድ ፍቃድ ሰይኖራቸው ነው ብለዋል፡፡

እንጀራው የሚጋገርበት ሁኔታም ንፅናውን የጠበቀ ባላመሆኑ በሂደት የሚከሰቱ የጤና እክሎችን ሊፈጥር እንደሚችል የተናገሩት አቶ አሰፋ በላይ ህብረተሰቡ ተመሳሳይ ተግባራትና አጠራጣሪ ሁኔታዎች ሲያገጥሙት ለሚመለከታቸው አካላት ጥቆማ መስጠት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

ምንጭ፦ የአ/አ ፖሊስ ኮሚሽን

@tsegabwolde @tikvahethiopia


Report Page