#ETH

#ETH


በሀዋሳ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች 12ኛ ክፍል አጠናቀው ወደ ዩኒቨርስቲ ከሚገቡ ተማሪዎችና ወላጆቻቸው ጋር የሶስትዮሽ ስምምነት መካሄድ ጀመረ፡፡

ስምምነቱ በመካሄድ ላይ የሚገኘው በሀዋሳ ከተማ ትምህርት መምሪያ አማካኝነት ሲሆን በዘንድሮው የትምርት ዘመን ዩኒቨርስቲ መግቢያ ነጥብ በማምጣት በሀገሪቱ ወደሚገኙ የተለያዩ ዩኒቭርስቲዎች ከሚያመሩ ተማሪዎች እና ወላጆቻቸው ጋር ነው፡፡

ስምምነቱም በዩኒቨርስቲ ህግጋት፣ መመሪያና ደንቦች ዙሪያ ለተማሪዎች እና ለወላጆቻቸው በየተማሩበት ትመህርት ቤት በሰለጠኑ አካላት ግልፅነት ከተፈጠረ ብኋላ የሚፈረም ይሆናል፡፡

በሰምምነቱ መሰረትም ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው ትምህርታቸውን አጠናቀወ ለመመረቅ ትምህርት ቤቶቹ የሚጠይቁትን ዝቅተኛ ነጥብ ከሟሟላት ባለፈ ዩኒቨርስቲዎቸ አለምአቀፍ ተቋማት መሆናቸውን ማመንና መቀበል፣ በዘር በብሔር፣ በሐይማኖት፣ በቀለም ወዘተ ሳይከፋፈሉ ተቻችለውና ተከባብረው የሚማሩበት መሆኑን ለመቀበል ዝግጁ የመሆን ግዴታ እንዳለባቸው ተቀምጧል፡፡

ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ ቆይታቸው ሊያጋጥሟቸው በሚችሉ ችግሮች ዙሪያ ጥያቄዎች ሲኖራቸው ጥያቄዎቻቸውን በአግባቡ እና በተወካዮቻቸው አማካኝነት የማንሳት ግዴታ እንዳለባቸው በስምነቱ ወቅት ግንዛቤ ከመፈጠሩ በተጨማሪ ሁከት እና ግጭት ባለመፍጠርና ባለመሳተፍ ለትምህርታቸው ብቻ ቅድሚያ የመስጠት ግዴታ እንዳለባቸውም ተቀምጧል፡፡

የትምህርት ቤቶቹን መሪ እሴቶች መከተል፣ ለመምህራን እንዲሁም ለአስተዳደር ሰራተኞች መታዘዝ ግዴታዎች ሲሆኑ፤ ንፅህና፣ የፀጉር አያያዝና ስርዓቱን የጠበቀ አለባበስ ከተማሪዎች የሚጠበቅ ከመሆኑ በተጨማሪ ማኛውም ኮፍያ፣ ቆብ የመሳሰሉ ከሀኪም ትዕዛዝ ውጭ የሆኑ ሌሎች ተጨማሪ ነገሮች በሙሉ የተከለከሉ መሆኑን ከወዲሁ ማወቅ እንዳለባቸውም በስምምነቱ የተገለፀ ነው፡፡

ለማንኛውም ወንድ ተማሪ ፀጉርን ከ1.5 ሳ.ሜ ሳያስበልጥ የመቆረጥ ግዴታ የተጣለበት ሲሆን ምንም አይነት የተለየ እና ወጣ ያለ ቅርፅ ማስያዝ በፍፁም የተከለከለ ሲሆን ለሴት ተማሪዎች ደግሞ ፀጉርን የተለየ ቀለም መቀባት የተከለከለ ነው፡፡

ተተልትሎ የሚሸጥ ሱሪ መልበስና የውስጥ ሱሪን የሚያሳይ አለባበስ የተከለከለ መሆኑ በሶስትዮሽ ስምምነቱ ከተካተቱ ሀሳቦች መካከል ናቸው፡፡

ምንጭ፦ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር

@tsegabwolde @tikvahethiopia

Report Page