#ETH

#ETH


በድሬዳዋ መስከረም አንድ የተቀሰቀሰ ግጭት ትናንት እና ዛሬ ተባብሶ መቀጠሉን የከተማዋ ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናገሩ። በግጭቱ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ሰዎች መቁሰላቸውን የገለጹት ነዋሪዎች የሕዝብ መጓጓዣም አገልግሎትም መቋረጡን የግብይት ማዕከላት መዘጋታቸውን ተናግረዋል። «የሀገር ሽማግሌዎች በየሰፈሩ እየዞሩ ይኸን ጉዳይ ለመቅጨት ጥረት እያደረጉ ነው» ያሉ አንድ የከተማዋ ነዋሪ ግጭቱ ሊባባስ ይችላል የሚል ሥጋታቸውን ገልጸዋል።

በድሬደዋ ከተማ ከአዲስ አመት በዓል ጀምሮ ደቻቱ እና አምስተኛ በተባሉ ሰፈሮች የጀመረው ግጭት ትናንትና ዛሬ ተባብሶ መቀጠሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፁ ፡፡ የተለያዩ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱንም ተናግረዋል ፡፡በከተማይቱ ሁለት አካባቢዎች ከአዲሱ ዓመት ዋዜማ ጀምሮ ለቀናት ጋብ ብሎ የቆየው ግጭት ትናንትናና ዛሬ ተባብሶ መቀጠሉን ለጀርመን ራድዮ አስተያየት የሰጡ ነዋሪዎች ገልፀዋል፡፡አንድ ሌላ አስተያየት ሰጪ በበዓል ዋዜማ የተቀሰቀሰውን ግጭት እዛው ማቆም እየተቻለ እንዲቆም ያልተደረገው ሁከት እንዲፈጠር የሚፈልጉ አካላት ስላሉ ነው ብለዋል ፡፡በከተማዋ ሁለት አካባቢዎች የተፈጠረው ግጭት አቅራቢያ ወደሆኑ ሌሎች አካባቢዎች መቀጠሉና ሁኔታው ከባድ መሆኑን የተናገሩት አስተያየት ሰጪ በግጭቱ በርካቶች መጎዳታቸውን ጠቁመዋል፡፡ በደቻቱና አምስተኛ ሰፈሮች ትናንት ጀምሮ በተቀሰቀሰው ግጭት ሳቢያ የንግድ እና የከተማ ትራንስፖርት እንቅስቃሴ ቆሟል፡፡ በአካባቢዎቹ የተፈጠረው ግጭት ከሰዓት ወዲህ ውጥረቱ በመከላከያና በሌሎች የፀጥታ አካላት መኖር ረገብ ቢልም አሁንም ውጥረት መኖሩንና ይህንኑ ለማርገብ የአካባቢው ሽማግሌዎች ለማምጣት ጥረት እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ተናግረዋል ፡፡ በተጠረው ግጭት ዙርያ የፖሊስንም ሆነ የሌሎች መንግስት አካላትን አስተያየት ማካተት አልተቻለም፡፡

VIA #DW

Report Page