#ETH

#ETH


ዮ- ማስቃላ በዓልን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ

የጋሞ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ተሻለ ማናዬ መስከረም 13/2012 ዓ.ም የሚከበረውን የዮ-ማስቃላ በዓልን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

የዮ- ጋሞ ማስቃላ ዋና ዓላማው የጋሞ አባቶች ለሠላም ተምሳሌት ሆነው የበጎ ሰው ልዩ ተሸላሚ መሆናቸውን ለመዘከርና አርዓያነታቸውን ለወጣቱ ትውልድ የሚተላለፍበት እና ዞኑ ለስፖርት በተለይም ለአትሌትክስ ስፖርት ያለውን ምቹ የአየር ሁኔታ በመጠቀም ተተኪ አትሌቶችን ከዞኑ ለማፍራት እንዲቻል ከ‹‹ ፋን ኢትዮጵያ›› ጋር በመሆን የ8 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ይካሄዳል፡፡

በዕለቱ የዮ-ማስቃላ የቋንቋና ስነ-ጥበብ ፌስቲቫል እንዲሁም የባህል ሲምፖዚዬም ይካሄዳል፡፡ ይህም በዞኑ ውስጥ የሚገኙትን የቱሪዝም ሀብቶቻችንን ለማስፋፋት ፣ ለማልማት ፣ ለማሳደግ እና ለማበልጸግ ዓላማ ያለው ነው፡፡

‹‹ፋን ኢትዮጵያ›› ከጋሞ ዞን አስተዳደር እና ከአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር ከዞናችን ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት የሚረዳ የሀገራችን ታዋቂ አትሌቶች የሚሳተፉበት የ8 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ይካሄዳል፡፡

የቱሪዝም ልማታችንን ለማፋጠንና ለማሳደግ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ፣ የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ በተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ የጋሞ ፣ የዘይሴ እና የጊዲቾ ብሔረሰብ አባላት እንዲሁም ሌሎች የሀገራችን ብሔር ብሔረሰቦች ተከባብረው ፣ ተፈቃቅረው እና ተስማምተው ፣ የሚያከብሩት በዓል እንደሆነ ምክትል አስተዳደሪው ተናግረዋል፡፡

የዘንድሮው የዮ ማስቃላ በዓል በድምቀት ሲከበር በዋናነት ታሳቢ ተደርጎ የሚሰራው ባህሉን በዓለም ደረጃ እንዲታወቅ እና በ UNESCO እንዲመዘገብ ለማስቻል ነው፡፡

እንደ አቶ ተሻለ ገለጻ የዘንድሮውን ዮ-ማስቃላ በዓል ለየት የሚያደርገው የቱሪዝም ተደራሽነታችን ለማሳደግ የተለያዩ የውጭ ሀገራት አምባሳደሮች ፣ የፌደራል ከፍተኛ ባለስልጣናት ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፣ የዞኑ አስራ ስምንት መዋቅሮች በዓሉ ላይ የሚሳተፉበትና የተለያዩ የቱሪስት መስህቦችን ይጎበኛሉ፡፡

Report Page