#ETH

#ETH


ጠሚር ዐቢይ አሕመድና የኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በጋራ በመሆን ዛሬ መስከረም 10 ቀን 2012 ጠዋት ከአባ ገዳዎችና ሌሎችም የሀገር ሽማግሌዎች ጋር የመጪውን ኢሬቻ በዓል አከባበርና በተጨማሪ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል::

ውይይቱም በተለይ የኢሬቻ በዓል የኦሮሞ ባህል እሴትና መርሕ በሆኑት የአንድነት፣ የፍቅርና የይቅርታ መሠረቶች ላይ በመመርኮዝ በሰላማዊ መንገድ መከበር እንዳለበት ተወስቷል:: አባ ገዳዎቹና የሀገር ሽማግሌዎቹ ይህንኑ ክብረ በዓል በሰላማዊ መንገድና ሁሉም ኢትዮጵያውያን በአንድነት የሚያከብሩት የደስታ በዓል እንዲሆን ባለድርሻ አካላት እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርበዋል::

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ እና ም/ር/መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የክልሉን ነዋሪዎችን የሚመለከቱ የልማት፣ የሰላምና፣ ለዉጡን የማስቀጠል ስራዎች ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዉ ከአባ ገዳዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ጋር መግባባት ላይ ደርሰዋል::

በተጨማሪም ከመላ ኢትዮጵያውያን ጋር በመናበብ እሴትን: ቋንቋንና የኦሮሞ ህዝብ ባህልን የበለጠ ለማሳደግ እንደሚሰራም ተገልጿል::

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድም የኢሬቻ በዓል ዝግጅትና አከባበር ሰላማዊና ብሄራዊ አንድነታችንን ባንጽባረቀ መልኩ እንዲሆን ምኞታቸዉን ገልጸዋል::

Report Page