#ETH

#ETH


መኮ)የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዶክተር ዳንኤል በቀለ ከደ/ብ/ብ/ሕ/ክ ከሚገኙ የመንግስት ካላት፣ ከግል ሚዲያ ተቋማት፣ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች አመራሮች ጋር በወቅታዊ የሰብአዊ መብት ጉዳዮች ዙሪያ ከመስከረም 06 እስከ 08/2012 ዓ.ም. ውይይት ያደረጉ ሲሆን ሁሉም አካላት የየራሳቸውን ድርሻ መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡ በተለይም የሲዳማ ብሔር ክልል የመሆን ጥያቄን ተከትሎ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህዝበ ውሳኔን የማስፈጸም ሂደት የሰብአዊ መብት ጥሰት መንስኤ እንዳይሆን የክልሉ መንግስት፣ የሚዲያ ተቋማት፣ የሲቪል ማህበራት እና ተፎካካሪ ፓርቲዎች ከኃይማኖት መሪዎች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከወጣቶች እና አጠቃላይ ከህብረተሰቡ ጋር ተከታታይ ውይይት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው እና ኮሚሽኑም በተሰጠው ኃላፊነት መሰረት የራሱን ሚና እንደሚጫወት ከመግለጻቸውም በተጨማሪ የኮሚሽኑን እገዛ ለሚጠይቅ አካል ፈጣን ምላሽ እንደሚሰጥ ቃል ገብተዋል፡፡

ዋና ኮሚሽነሩ በክልሉ ከተፈጠረው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ ግንኙነት እንዳላቸው ተጠርጥረው በፖሊስ ጣቢያ ከሚገኙ ተጠርጣሪዎች ጋርም ስለአያያዛቸው፣ እና ስለፍርድ ቤት ሂደቱ ውይይት አድርገዋል፡፡

ዋና ኮሚሽነሩ በኮሚሽኑ የሥራ እንቅስቃሴ ተግዳሮት በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ እንዲሁም ወደፊት መከናወን ስላለባቸው ጉዳዮች ከሐዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሰራተኞች ጋር ሰፊ ምክክር አድርገዋል፡፡

Report Page