#ETH

#ETH


"የኢሬቻ በዓል ከግል ፍላጎታችን በላይ ነው!" አቶ ሽመልስ አብዲሳ

የኢሬቻ በዓልን ከኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ጋር በጋራ ማክበር ለኦሮሞ ህዝብ ክብር እና ድል ነው አሉ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ። የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በዛሬው እለት የ2012 የኢሬቻ በዓል ዝግጅትን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ አቶ ሽመልስ አብዲሳ በመግለጫቸውም የኦሮሞ ህዝብ ለረጅም ዓመታት ተቋርጦ የነበረውን የአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻን ዘንድሮ ማክበር መቻሉ ልዩ እንደሚያደርገው ገልፀዋል። የዘንድሮውን የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ ከኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ጋር በጋራ ማክበር መቻሉም ለኦሮሞ ህዝብ ክብር እና ድል ነው ሲሉም አስታውቀዋል።

የኢሬቻ በዓል ከግል ፍላጎታችን በላይ ነው ያሉት አቶ ሽመልስ፥ ዘንድሮ በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ እና በቢሾፍቱ ሆራ ሀርሰዴ ለሚከበሩ በዓላት አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት መደረጉንም ጠቅሰዋል። በአዲስ አበባ እና ቢሾፍቱ በሚከበሩ የኢሬቻ በዓላት ላይ የሚሳተፉ የኦሮሞ ህዝቦች ባህላዊ አልባሳትን ለብሰው በበዓላቱ ላይ እንዲሳተፉም ጥሪ አቅርበዋል።

ሌሎች የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች እና ህዝቦችም በባህል አልባሳቶቻቸው ደምቀው በዚህ የሰላም እና ፍቅር በዓል በሆነው ኢሬቻ ላይ ይካፈላሉም ብለዋል ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ አቶ ሽመልስ አብዲሳ በመግለጫቸው። የኢሬቻ በዓል በተሳካ መልኩ እንዲካሄድም መላው ህዝብ እና ወጣቶች የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።

Via #FBC

@tsegabwolde @tikvahethiopia

Report Page