#ETH

#ETH


የዓለም መንግስታት ለአየር ንብረት ለውጥ ድርጅት ስብሰባን መሰረት በማድረግ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተቃዋሚዎች የአየር ንብረት ለውጥን አስመልክቶ ሰልፍ መውጣታቸው ተዘግቧል፡፡

እየተስተዋለ ያለውን የዓለም የአየር ንብረት መዛባት ጉዳይ ጉዳዬ ያሉ የተለያዩ ሀገራት ተማሪዎች “ተለዋጭ ፕላኔት የለንም’’ በሚል ሃሳብ ተቃውሟቸውን ገልፀዋል፡፡

በጎርፍ እየተጥለቀለቁ ያሉ የፓስፊክ ደሴቶች፣ ኒው ዚላንድ፣ የአውስትራሊያ፣ የባንኮክ እና የታይላንድ ሰልፈኞች የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስን ለማቃለል የዓለም መንግስታት አስቸኳይ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በዓለም ከፍተኛ የድንጋይ ከሰል እና የተፈጥሮ ጋዝ ወደ ውጭ በምትልከው አውስትራሊያ ብቻ መንግስት በ2030 የካርቦን ልቀትን ኢላማ እንዲያደርግ በ110 ከተሞች ውስጥ ሰልፉ ይካሄዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የተቃውሞ ሰልፉ ዛሬ በ150 ሀገሮች ለማድረግ የታቀደ ሲሆን የተባበሩት መንግስታት ዋና መስሪያ ቤት በሚገኝባት በኒው ዮርክ ከተማ ሰልፉ እንደሚጠናቀቅ ተጠቁሟል፡፡

በዘንድሮው የተባበሩት መንግስታት ስብሰባ የዓለም መሪዎች ከነዳጅ ወደ ታዳሽ የኃይል ምንጮች የሚደረገውን ጉዞ ጨምሮ የአየር ንብረት ለውጥ ቅነሳ ዙሪያ ለመወያየት እንደሚያሰባስብ ታውቋል፡፡

አሜሪካን ጨምሮ አውስትራሊያ እና በአንዳንድ ሀገሮች የአየር ንብረት ለውጥ ፖሊሲ የፖለቲካ መጫወቻ መሆኑ አሳሳቢ ነው የሚሉ ድምፆች እየተስተዋሉ ናቸው፡፡

በተለይም ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራንፕ በ2017 ሀገራት እየጨመረ የሚሄደውን የአየር ንብረት የሙቀት መጠን ለመቋቋም ከተፈረመው ስምምነት አሜሪካ መውጣቷን መግለጻቸው ይታወቃል፡፡

ምንጭ፡- አልጃዚራ

Report Page