#ETH

#ETH

Dave

አዲሱ የኤሌክትሮኒክስ ታክሲ ስምሪት ስርዓት!

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የኤሌክትሮኒክስ ታክሲ ስምሪትን በተመለከተ አዲስ መመሪያ በነሃሴ ወር መጠናቀቂያ ላይ ነበር ያፀደቀው። አዲሱ መመሪያ ከፈቀዳቸው አሰራሮች መካከል በኮድ 1 ታክሲ መመዝገብ የሚቻሉ ባለ ቢጫ ወይም ባለሰማያዊ ቀለም ታክሲዎች ሊሆኑ እንደሚችሉና ቴክኖሎጂ አግዟቸው በኤሌክትሮኒክስ ስርዓት ቁጥጥር ሊደረግባቸው የሚችሉ ታክሲዎች ሆነዋል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የከተማው የኢኮኖሚክ ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርት ቢሮ ሃላፊው ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ ለሸገር ራድዮ በሰጡት ማብራሪያ ከዚህ ወዲያ ለሚተገበረው መመሪያ ይህን ብለዋል፦

"የኤሌክትሮኒክስ ታክሲ ስምሪት ስርዓት የሚባል መመሪያ ወጥታል። የወጣው መመሪያ ከዚህ በፊት መጠቀም ሚችሉም ናይችሉም የሚለያይ ነበረ አሁን ግን ማንም ሰው መጠቀም የሚችልበት ከዚህ በፊት አግደን የነበረው አገልግሎት ክፍት ያደረግንበት መመሪያ ነው። ከዚህ በፊት ተከልክለው የነበሩ አገልግሎቶች ክፍት ያደረገ አዲስ መመሪያ ነው። ...ከዚህ በፊት ኮድ 1 ታክሲ መስጠት ተከልክሎ ነበር ስለዚህ ይህ መመሪያ ኮድ ኣንድ ታክሲ ማውጣት እንዲቻል ፈቅዶ የወጣ መመሪያ ነው። ማንም ሰው ሄዶ ኮድ 1 ታክሲ አውጥቶ...ሰማያዊና ነጭ ቀለም ሊሆን ይችላል ቀብቶ መንቀሳቀስ እንዲችል የፈቀድንበት ነው። ስንፈቅድ ግን ወደ ኤሌክትሮኒክ የታክሲ ስምሪት ሲስተም ውስጥ እንዲገቡ የሚያደርግ ነው። ወደዛ ከገቡ ገብተው ለመስራት ፍቃደኛ ከሆኑ በስልክ ጥሪ፣ ማስተናገድ ፍቃደኛ ከሆኑ ይሄ ተከልክሎ የነበረውን የሚፈቅድ መመሪያ ነው።" 

የኤሌክትሮኒክስ ታክሲ ስርዓትን ቀደም ብለው የጀመሩትም ሆነ ወደፊት ለመሰማራት ላሰቡ ድርጅቶች አሁን የተሰናዳው መመሪያ ጥርጊያውን ያቀናላቸዋል ብለዋል የትራንስፖርት ኃላፊው። የከተማ አስተዳደሩ ኮድ 1 ፍቃድን ከመስጠት ከታቀበበት ምክንያቶች ዋነኛው ታክሲዎቹን ለመቆጣጠር የሚያማች ስርዓት ባለመኖሩ ተሳፋሪዎች ስጋት ላይ በማውደቃቸው ነበር የሚሉት ዶ/ር ሰለሞን ታክሲዎቹ ተወዳዳሪ ናቸው ለማለትም ይቸግራል ነው ያሉት። አዲሱ ህግ አስገዳጅናት እንዳለውም የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊው ተናግረዋል። ማንም ሰው በኮድ 1 ፍቃድ ማውጣት ይችላል፤ ነገር ግን በኤሌክትሮኒክስ ስርዓት ስምሪቱን በሚቆጣጠሩ ድርጅቶች ውስጥ ገብቶ ለመስራት ፈቃደኛ መሆን ይጠበቅበታል ብለዋል።

"ማንም ሰው ወደታክሲ መግባት ይችላል የሚችለው ግን ኮድ 1 ሆኖ ነው። ኮድ 1 ተፈቅዷል ለማንም ሰው ዝግ አይደለም። ግን ይሄንን የሚያደርገው የኤሌክትሮኒክስ ስርዓት ስምሪቱን በሚቆጣጠሩ ድርጅቶች ውስጥ ገብቶ ለመስራት ፍቃደኛ ከሆነ ብቻ ይሆናል። ሰው ደግሞ ያንን መግባት ስላቃተው ነው ተደብቆ በኮድ 2 እና 3 የሚሰራው ኮድ 1 ጠይቆ ስለተከለከለ ነው። አሁን ግን ክፍት ሆኗል። . . . እየፈራ፣ እየተደበቀ የሚመጣው ብቻ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ በነፃነት ደስ ብሎት መስራት የሚችልበትን ነው"

በሌላ በኩል...

አሁንም ቢሆን በኤሌክትሮኒክስ የታክሲ ስርዓት ውስጥ የተካተቱ አሽከርካሪዎች ከድርጅቱ የሚጠየቁት የጥቅም መጋራት በመቶኛ ከፍተኛ እንደሆነ ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ ገልፀዋል። እስከ 17% ክፍያ የሚጠየቁ ባለታክሲዎች መኖራቸውን ያነሱት ዶክተሩ፤ አዲሱ መመሪያ ለዚህ ጉዳይ የተሻለ መደራደሪያ ይፈጥራል ብለዋል።

"በኤሌክትሮኒክስ ታክሲ ስምሪት ውስጥ ሆነው የሚሰሩ ሰዎች አንዳንዴ የሚጠየቁት ፐርሰንቴጅ በጣም ብዙ ነው። ምንም ነገር በመኪናቸው፣ በነዳጃቸው፣ በመለዋወጫ እቃቸው፣ እራሳቸው ሰርተው 17% ይሰጣሉ በጣም fair አይደለም። አማራጭ ስለሌላቸው ነው ይሄን የሚያደርጉት እኛ ደግሞ ፈቀድንላቸው ታክሲ ካደረግናቸው ነፃነት አላቸው መርጠው ማድረግ ይችላሉ ስለዚህ በተሻለ ዋጋ መደራደር ይችላሉ፤ መርጠው የወደዱት ጋር መስራት ይችላሉ። ለነሱም ደግሞ የተሻለ መስራት የሚችሉበት ነው። ይሄ መሆኑ ደግሞ ብዙ ሰው ፈርቶ ቁጭ ያለው ወደዚህ እንዲመጣ ማድረግ ይችላል ማለት ነው። ...መንግስትም በአግባቡ ሚቆጣጠረው ዘርፍ መሆን ይችላል። ...በኮድ 2 እና በኮድ 3 ህግ የለም፤ ታክሲ መስራት ህግ የለም የፌደራል አዋጁ ይከለክላል።"

NB. አዲስ የተዘጋጀውን የኤሌክትሮኒክስ ታክሲ ስምሪት ስርዓትን በተመለከተ የከተማ አስተዳደሩ ነገ ማብራሪያ ይሰጣል።

✍TIKVAH-ETHIOPIA

Via ShegerFM 102.2

@tsegabwolde @tikvahethiopia

Report Page