#ETH

#ETH


የግብጹ ፕሬዘዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ኢትዮጵያ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን የጀመረችው አሁን ቢሆን እንድትገነባ አንፈቅድላትም ነበር አሉ።

ፕሬዘዳንቱ ኢትዮጵያ ከ8 ዓመት በፊት የተካሄደውን የግብጽ አቢዮት ተጠቅማበታለች ሲሉ ተናግረዋል።

ፕሬዘዳንቱ ይሄንን ያሉት በትላንትናው እለት በካይሮ በተደረገ ብሔራዊ የወጣቶች መድረክ ላይ ነው።

ግብጻዊያን ከ8 ዓመት በፊት የሆስኒ ሙባረክን አገዛዝ ለመገርሰስ ወደ አደባባይ በወጡበት ወቅት ኢትዮጵያ ይሄነን አጋጣሚ በመጠቀም የህዳሴውን ግድብ መጀመሯን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የህዳሴውን ግድብ የጀመረችው አሁን ቢሆን ኖሮ እንከለክላት ነበር ሲሉ ለተሰብሳቢዎቹ መናገራቸውን የአገሪቱ የህትመት ሚዲያ አህራም ኦን ላየን የተሰኘው የእንግሊዘኛ ጋዜጣ አስነብቧል።

ግብጽ በአብዮቱ ጊዜ የሰራችው ስህተት ዋጋ እያስከፈላት ነው ያሉት ፕሬዘዳንት አልሲሲ ተመሳሳይ ስህተት ለመስራት የሚፈልጉ ግብጻያን ወጣቶች እንዳሉም ተናግረዋል።

ይሁንን የፕሬዘዳንቱ ንግግር እየደረሰባቸው ያለውን ተቃውሞ ለማቀዝቀዝ ነው የሚል ትችት እየደረሰባቸው ይገኛል።

ፕሬዘዳንቱ ይሄንን ያሉት የኢትዮጵያን ህዳሴ ግድብ ለአገር ውስጥ ፖለቲካ የመጠቀም ፍላጎት ስላላቸው ነውም እየተባሉ ይገኛሉ።

ፕሬዘዳንት አልሲሲ ስልጣናቸውን እስከ 2034 ድረስ የሚያራዝምላቸውን ህገ መንግስት በአገሪቱ ፓርላማ ማጸደቃቸውና በሰብዓዊ መብት ጥሰት ትችቶችን በማስተናገድ ላይ ናቸው።

ግብጽ ኢትዮጵያ የህዳሴው ግድብ የውሃ ሙሌት ጊዜ ወደ ሰባት ዓመት ከፍ ይበልልኝ፣የግድቡን ሁኔታ የሚከታተል በካይሮ እና በአዲስ አበባ ቢሮ ይከፈትና ሌሎች ጥያቄዎችን ማንሳቷ ይታወሳል።

ኢትዮጵያ የግብጽን አዲስ አቋም ፈጽሞ እንደማትቀበልና ግድቡ በታችኛው ተፋሰስ አገራት ላይ የከፋ ጉዳት እንደማያደርስ በተደጋጋሚ አስታውቃለች።

የኢትዮጵያ፣ግብጽና ሱዳን ብሔራዊ የቴክኒክ አማካሪ በያዝነው ሳምንት በካይሮ ወይም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ይጠበቃል።

የብሔራዊ ቴክኒክ ኮሚቴ ስብሰባ በኢትዮጵያና ሱዳን በተፈጠረው የፖለቲካ ቀውስ ምክንያት ተቋርጦ ቆይቷል።

ባሳለፍነው ሳምንት የሱዳይ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብደላ ሃምዶክ ከአዲሷ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ጋር ከግብጹ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሽኩሪ ጋር በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ በካርቱም ተወያይተዋል።

ከዚህ በፊት ሱዳንና ኢትዮጵያ በህዳሴው ገድብ ዙሪያ ተመሳሳይ አቋም መያዛቸው ያልተመቻት ግብጽ ውይይቱን በራሷ ፍላጎት ለማስኬድ የተለያዩ አማራጮችን በመከተል ላይ ትገኛለች።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም /በሳሙኤል አባተ/

@tsegabwolde @tikvahethiopia

Report Page