#ETH

#ETH


ማስታወቂያ!

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ ለ2012ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን ተቀብሎ በህክምና ዶክትሬት ዲግሪ (Medicine) ለማስተማር ይፈልጋል፡፡ 

የማመልከቻ መስፈርት፦

1. በ2011ዓ.ም በመደበኛ ትምህርት ፕሮግራም ሀገር አቀፍ ከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደው ትምህርት ሚ/ር በወሰነው መሰረት በአራቱ የትምህርት አይነቶች (እንግሊዘኛ፣ ሒሳብ፣ ፊዚክስ እና አፕቲቲውድ)

• ልዩ ትኩረት ከሚሹ ክልሎች እና ዞኖች /ጋምቤላ ፣ሶማሌ፣አፋር፣ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ደቡብ ኦሞ ዞን፣ምዕራብ ኦሞ ዞን ፣ቦረና ዞን እና ዋግምራ ዞን/

 ለወንዶች 245 እና ከዚያ በላይ

 ለሴቶች 225 እና ከዚያ በላይ

• ለአዲስ አበባ እና ሌሎች ክልሎች 

 ለወንዶች 265 እና ከዚያ በላይ

 ለሴቶች 245 እና ከዚያ በላይ, ውጤት ያለው/ያላት

2. ከ9-12ተኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ውጤት 80% እና ከዚያ በላይ ውጤት ያለው/ያላት

የማመልከቻ ጊዜና ቦታ 

• ማስታወቂያው በሚዲያ (በቴሌቪዥን) ከተነገረበት ቀን ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ ቀናት በኮሌጁ ድረ ገፅ http://197.156.83.153/admission/ መመዝገብ ትችላላችሁ::

• በተጨማሪ የማመልከቻውን ሊንክ (Link) ከኮሌጁ ድረ ገፅ https://www.facebook.com/sphmmc/ ማግኘት ይቻላል፡፡

• የጹሐፍ ፈተና የሚሰጥበት ቀን መስከረም 11/ 2012 ዓ.ም 

• ፈተና የሚሰጥበት ቦታ አዲስ አበባ ብቻ ሲሆን የመፈተኛ ጣቢያ በኮሌጅ ድረ ገፅ እና Facebook ይገለፃል፡፡

ማሳሰቢያ፦

• ቀጥሎ የተገለፁትን ለማመልከት የሚያስፈልጉ ዶክመንቶችን ስካን በማድረግ ማያያዝ ይጠበቅባችኋል

o የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤቶች 

o ከ9-12 ክፍል ትራንስክሪፕት  እና

o የመመዝገቢያ ክፍያ 50 ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሂሳብ ቁጥር -1000208431068  ገቢ የተደረገበትን ደረሰኝ 

o ከዚህ ቀደም የተመዘገባችሁ አዲሱን መስፈረት የምታሟሉ ከሆነ በደጋሚ እንደ አዲስ ክፍያ ሳይከፍሉ ማመልከት ይቻላል፡፡

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ ሪጅስተራር

ጽሕፈት ቤት

@tsegabwolde @tikvahethiopia

Report Page