#ETH

#ETH


የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ በ2011 በጀት ዓመት ብቻ 186 እና እስካሁን ደግሞ የ2011ዱንም ጨምሮ በጠቅላላው 425 አምቡላንሶች በላይ ተሰራጭተው አገልግሎት በመስጠት ላይ ቢሆኑም ችግሮች እየተስተዋሉባቸው ይገኛል፡፡

የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ የሚሰጠው ማህበራዊ አገልግሎት እጅግ ከፍተኛና ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ የጤና ተግባራትን በማሳካት ሁለተኛውን ዙር የጤናውን ሴክተር ትራንስፎርሜሽን አጀንዳዎችን ለማሳካት ብርቱ ርብርብ ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ከሚሰሩት ስራዎች ውስጥ አንዱና በከፍተኛ ትኩረት እየተከወነ ያለው ስራ፤ ውስን መሻሻልና ለውጥ የመጣበት ቢሆንም ጨርሶ ማስወገድ ያልተቻለውና አሳሳቢው ስራ ከወሊድ ጋር በተያያዘ የሚሞቱ እናቶች ጤና ጉዳይ ነው፡፡ ይህንንም ችግር ለመቅረፍ መንግስት፣ ህብረተሰቡና የጤና ልማት አጋሮች ባደረጉት ሰፊ እንቅስቃሴ እናቶች ቤት ውስጥ ከመውለድ ተላቅቀው በጤና ተቋማት ( ጤና ጣቢያና ከዚያ በላይ ባሉ የጤና ተቋማት) በሰለጠነ ባለሙያ ድጋፍ አግኝተው እንዲወልዱ ማድረግ ዋነኛው ነው፡፡ ስለሆነም ይህንን የጤና ተቋም ወሊድ ለመደገፍ ይቻል ዘንድ የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ከጤና ሚንስተር ጋር በመተባበር እና ከህብረተሰቡ በተሰበሰበ መዋጮ የተገዙ በ2011 በጀት ዓመት ብቻ 186 እና እስካሁን ድረስ የ2011ዱንም ጨምሮ በጠቅላላው 425 አምቡላንሶች በላይ በማስመጣት ለወረዳዎች እንዲደርሱ በማድረግ እና የአምቡላንስ አገልግሎት አጠቃቀም አሰራር በማዘጋጀት አገልግሎት በመስጠታቸው በሰለጠነ ባለሙያ የሚሰጠውን የተቋም ወሊድ በከፍተኛ ሁኔታ ማሻሻል መቻላቸውና የእናቶችን ሞት ለመቀነስ የሚደረገውን ርብርብ በከፍተኛ ሁኔታ ማገዝ መቻላቸው ይታወቃል፡፡ ሆኖም ግን አንዳንድ ወረዳዎችና ተቋማት አምቡላንሶቹ ከተገዙበት ዓላማ ውጭ እናቶች ተቋም መድረስ ሳይችሉ ለተለያዩ የጤና ችግሮችና ሞት እየተዳረጉ ባሉበት ሁኔታ መንገድ ላይ ምጥ ከበረታባቸው የሚገለገሉበትን የማዋለጃ አልጋና ሌሎች ተያያዥ መሳሪያዎችን ከአምቡላንሱ ላይ በማስነሳት እና በተጨማሪም አልጋውም መሳሪያዎቹም እያሉ በአምቡላንስ አጠቃቀም መኑዋሉ ላይ በግልጽ በተቀመጠው መሰረት ለማይፈቀዱ የተለያዩ ተግባራት በማዋል ላይ ስራው ላይ ችግር እየፈጠሩ ይገኛሉ፡፡ ከእነዚህም ወረዳዎች መካከል ደንባ ጎፋ ወረዳ አንዱ በመሆን ከዚህ ቀደም ያጋጠማቸውን ችግር በመጥቀስ አምቡላንሱን ለትራንስፖርት ሰርቪስ እንዲሰጥ በካቢኔ ወስነው በደብዳቤ ለጤና ጽ/ቤቱ ማሳወቃቸውን ደብዳቤውንም ጭምር ፖስት በማድረግ በበርካታ አካውንቶች ላይ ፌስቡክን ጨምሮ ፖስት የተደረገውን ቢሮውም ተመልክቶት ውይይት ተደርጎበት ጉዳዩ መጣራት እንዳለበት ተወስኗል፡፡

በመሆኑም ጉዳዩን እስከወረዳው ድረስ በመንቀሳቀስ የሚያጣራ ኮሚቴ የሰየመ ሲሆን ከነገ መስከረም 3 ቀን 2012 ጉዳዩን አጣርቶና የማረሚያ ዕርምጃ በመውሰድ የሚያሳውቅ መሆኑን ያሳውቃል፡፡

የደ/ብ/ብ/ህ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ

Report Page