#ETH

#ETH


በአዲስ አበባ በተለምዶ አፍንጮ በር በሚባለው አካባቢ ዛሬ እኩለ ቀን ላይ ግንብ ተደርምሶ በመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት አደረሰ።

አደጋዉ ሁለት መኖሪያ ቤቶችን ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ዉጭ ያደረገ ሲሆን ሌሎች 6 የሚሆኑትን ደግሞ በከፊል እንደጎዳ ነዋሪዎች ለኢዜአ ተናግረዋል።

በወረዳው  88 ቤቶች ለአደጋ ተጋላጭ መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

በአደጋው  ቤታቸውና ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ መውደሙን ወይዘሮ አዜብ ሞገስ  የተባሉ ነዋሪ ገልፀዋል።

አደጋ ከመድረሱ በፊት በአካባቢው የአደጋ ስጋት መኖሩን ከወረዳ እስከ ክፍለ ከተማ በተደጋጋሚ አቤቱታ በማቅረብ ከቦታው ተነስተው ተለዋጭ ቤት እንዲሰጣቸው ጠይቀው እንደነበርም ተናግረዋል።

አክለውም መንግስት የደረሰባቸውን ችግር በመረዳት ቤተሰባቸውን የሚያኖሩበት ቤት እንዲሰጣቸዉና ለእለት ፍጆታ የሚሆን  የምግብ እርዳታ እንደያደርግላቸውም ጠይቀዋል።

ተመሳሳይ ጉዳት የደረሰባቸው አቶ ንጉሴ ሰይፋ  በበኩላቸው ግንቡ መፍረስ ከጀመረ ከሶስት አመት በላይ እንዳስቆጠረ ገልጸዋል።

የክፍለ ከተማ እና ወረዳ አመራሮች ከአስር ጊዜ በላይ መጥተው ቢመለከቱትም ከማየት ያለፈ መፍትሄ ባለመስጠታቸው ለአደጋ መዳረጋቸውን ተናግረዋል።

በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ አምስት ምክትል ስራ አስፈፃሚና የቤቶች ልማት ሃላፊ አቶ ፀጋዬ ነጋሽ በበኩላቸው የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት ያሉ አማራጮችን በማጤን አፋጣኝ ምላሽ እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

በወረዳው  88 ቤቶች ለአደጋ ተጋላጭ መሆናቸው መለየቱን የሚገልፁት አቶ ፀጋዬ ችግሩን በወረዳ ደረጃ ብቻ መፍታት ስለማይቻል ለሚመለከታቸው አካላትም ጭምር አሳውቀናል ብለዋል።

የችግሩን ሁኔታ የአራዳ ክፍለ ከተማ ፣  ለከተማው መንገዶች ባለስልጣን እና  የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች  እንዲያውቁት መደረጉንም።

ተጎጂዎቹ የሚመለከተው አካል አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው አበክረው ጠይቀዋል።

#ena

Report Page