#ETH

#ETH


በጫንጮ ከተማም 456 ኪሎ ግራም ቅቤ ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅለው ለገበያ ሊያቀርቡ የነበሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ዳንኤል አረጋ ለኢዜአ እንዳሉት ቅቤን ከባዕድ ነገር ጋር ቀላቅለው ሲሸጡ ነበሩ ሁለት ግለሰቦች የተያዙት በትናንትናው ዕለት ነው፡፡

ግለሰቦቹ የተያዙት በዓሉን ምክንያት በማድረግ የከተማው ፖሊስ ለነዋሪው አስቀድሞ በፈጠረው ግንዛቤ መሰረት ከነዋሪዎች ለፖሊስ በደረሰ ጥቆማ ነው።

“ፖሊስ በአሁኑ ወቅት በግለሰቦቹ ላይ ምርመራ የጀመረ ሲሆን ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙ ይደጋል” ብለዋል።

የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅና በዓሉ በሰላም እንዲከበር የከተማው ፖሊስ ከክልሉ ልዩ ኃይሎች፣ ከመከላከያ ሠራዊትና ከፈዴራል ፖለስ አካላት ጋር በቅንጅት እየሠራ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

ህብረተሰቡ ላደረሰው ጥቆማ አመስግነው በቀጣይም ማንኛውም ወንጀል ሲፈጸም በፍጥነት ለፖሊስ ጥቆማ በማድረግ የበኩላቸውን እንዲወጡ አስገንዝበዋል፡፡

በተመሳሳይ ዜና በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ጫንጮ ከተማ 456 ኪሎ ግራም ቅቤ ከባዕድ ነገር ጋር አቀላቅለው ለገበያ ሊያቀርቡ የነበሩ ሁለት ግለሰቦችን መያዛቸውን የከተማው ፖሊስ አስታውቋል።

የከተማው ፖሊስ የኮሙዩኒኬሽን ዲቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ታዴዎስ ዘውገ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት ግለሰቦቹ የተያዙት በሰሌዳ ቁጥሩ 3-57774 ኦ.ሮ አይሱዙ የጭነት መኪና ጨለማን ተገን አድርገው ከጐጃም ወደአዲስ አበባ ለማስገባት ሲሞክሩ ነው።

ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ በመታገዝ ከሌሎች ሸቀጦችና ኬሚካል ጋር ለሰው ጤና ጐጂ በሆነ መልኩ ተጭኖ ሲጓዝ የነበረውን ቅቤ መያዙን ኮማንደር ታዴዎች ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የቅቤው ናሙና ለኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ተልኮ ለሰው ጤና ጐጂ መሆኑንና ከባዕድ ነገሮች ጋር መቀላቀሉን በምርመራ እንደተረጋገጠ አመልክተዋል፡፡

“በቁጥጥር ሥር የዋሉት ግለሰቦች አስፈላጊውን ምርመራ በማድረግ በቅርቡ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ይደረጋል” ብለዋል።

ህብረተሰቡ በአልን ተንተርሶ ከሚደረግ ጥንቃቄ የጐደለው የምግብ ግዥ ራሱን መጠበቅ እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡

በተለይ በየመንደሩ እየተዘዋወሩ ቅቤና ማር የሚያቀርቡ ግለሰቦችን በተለየ ጥንቃቄ መገበያየት እንዳለበትና በተቻለ መጠን ተጠያቂነትና ኃላፊነት ከሚወስድ አካል ሊገዛ እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡

Via #ENA

Report Page