#ETH

#ETH


ህዝቡ አንድነቱን በማጠናከር ለየትኛውም ፈተና ሳይንበረከክ ለስኬት ሊሰራ ይገባል - አቶ ሽመልስ አብዲሳ

ህዝቡ አንድነቱን በማጠናከር ለየትኛውም ፈተና ሳይንበረከክ ለስኬት ሊሰራ እንደሚገባ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ።
አቶ ሽመልስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አዲሱን አመት በማስመልከት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፥ በ2012 ዓ.ም ለተሻለ ተጠቃሚነት ይሰራል ብለዋል።
በ2011 ዓ.ም የተገኙ ስኬቶችን በማጠናከርም ለ2012 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ህብረተሰቡ የድርሻውን ሊወጣ ይገባልም ነው ያሉት።
በቀጣዩ በጀት አመትም መንግስት ህዝቡን የተሻለ ተጠቃሚ ለማድረግ እንደሚሰራም አንስተዋል።
አዲሱ አመት ስኬታማ ስራዎች የሚሰሩበት፣ ሰላም የሚረጋገጥበት፣ የህግ የበላይነት ለማስከበር የሚሰራበት፣ ህዝቡን ከድህነት ለማውጣት የተጀመሩ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን የምናስቀጥልበት እና ስራ አጥ ዜጎች የተሻለ ስራ የሚያገኙበት እንደሚሆንም ተናግረዋል።
በፖለቲካው ዘርፍም በ2011 ዓ.ም የታዩ መልካም ስራዎችን በማስቀጠል ስኬታማ ስራዎች እንደሚሰሩም ገልጸዋል።
እንደ ኤፍ ቢ ሲ ዘገባ የህብረተሰቡ ኑሮ እንዲሻሻልም በኢኮኖሚው ዘርፍ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉም ነው ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ።
በየደረጃው ያለ የመንግስት አመራር የተያዙ እቅዶችን ለማስፈጸም በተጠያቂነት እንዲሰራም አሳስበዋል።
ባለፉት ሁለት የክረምት ወራት በዜግነት አገልግሎት የችግኝ ተከላን ሳይጨምር ከ1 ቢሊየን ብር በላይ የሚገመት ስራ መሰራቱንም አስረድተዋል።
በዚህም የህብረተሰቡ ተሳትፎ ከፍተኛ እንደነበር ጠቅሰው፥ ህብረተሰቡ ላደረገው ተሳትፎም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ይህ የህብረተሰቡ ተሳትፎ በ2012 በጀት አመት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቅሰዋል።

#ፈጣን_መረጃ

Report Page