#ETH

#ETH


 ”የኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስቲያን ለእኛ ኢትዮጵያዊያን ክብራችን ናት” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚስትሩ ይህን ያሉት ከሐምሌ 3 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በአገልጋይ ዮናታን አክሊሉ የተዘጋጀው የመልካም ወጣቶች ስልጠና ማጠቃለያ ትናንት በሚሊኒየም አዳራሽ ሲካሄድ ነው።

በመርሃ ግብሩ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣የገቢዎች ሚኒስትሯ አዳነች አበቤ እና ከሁሉም የአገሪቷ አካባቢዎች የመጡ ወጣቶች ተሳትፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በዚሁ ጊዜ ”በሄድንበት አገር ደረታችንን ነፍተን አንድ ሺህዓመት የቆየ ቤተክርስቲያን አለን ስንል ሌሎች ይደነቃሉ እኛ ግን አናከብራትም” ብለዋል።

ቤተክርስቲያኗ የፖለቲካና የዘር አጀንዳ መጠቀሚያ እየሆነች መምጣቷንም አንስተዋል።

ቤተ-ክርስቲያኗ በአገሪቷ ውስጥ ትልቅ አሻራ እንደሚኖራትና ከነክብሯ እንድትቀጥል እንደሚፈለግም ነው የገለጹት። አገልጋይ ዮናታን በበኩላቸው ”ኢትዮጵያ ድርና ማግ ሆና የተሰራችባት የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቅጥር ንዋየ ቅዱሳቶቿ ሲዘረፉና ሲቃጠሉ እንደሚገባን ያህል ፈጥነን ስላልደረስንላት በትውልዱ ስም ይቅርታ እጠይቃለሁ” ብለዋል።

የአገር የጤናና የትምህርት ባለውለታ ያሏትን የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንንም በሚገባ እገዛ ባለማድረጋችን ‘ይቅርታ እንጠይቃለን’ ነው ያሉት። ”እምነታችሁን እንደራስ ባለማየት ደግነታችሁን ትተን የማይሆን ስም የሰጠናችሁን ሙስሊም ወንድሞቻችን በትውልዱ ስም ይቅርታ እጠይቃለሁ” ብለዋል አገልጋይ ዮናታን።

VIA #ENA

Report Page