#ETH

#ETH


ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከአውሮፓውያኑ የ2019 የሔስያን የሰላም ሽልማት ያገኙትን 25 ሺህ ዩሮ ለመልካም ወጣት ማእከል ግንባታ አበረከቱ።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከአውሮፓውያኑ የ2019 የሔስያን የሰላም ሽልማት ያገኙትን 25 ሺህ ዩሮ ለመልካም ወጣት ማእከል ግንባታ አበረከቱ።ለሰባት ተከታታይ ዙር በዚህ ክረምት በሃዋሳ በአገልጋይ እና በመልካም ወጣት ፕሮጀክት መሪ ዮናታን አስትባባሪነት ሲካሄድ የነበረው መርሃ ግብር የመዝጊያ ስነ ስርዓት በሚሌኒየም አዳራሽ ዛሬ ተካሂዳል።በስነ ስርዓቱ ላይ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዝግጅቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት መልካም ወጣት ማለት ከማስመሰል ወደ መምሰል የሚያድግ መሆኑን ተናግረዋል።

ይህም ማለት ወደ እውቀት፣ ጥበብና ፍቅር ወደ መስጠት ማደግ ነው ብለዋል።ሱስ ሀሺሽ ብቻ አደለም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ዘርን ከዘር እና ሀይማኖትን ከሃይማኖት ማባላትም ሱስ ነው ብለዋል።የውሸት፣ የዘረኝነት እና የዳተኝነት ብዙ ሱሰኛ ባሉበት ሀገር እናንተ ለማስተማሪያነት ተመርጣችኋል ብለዋል።የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን የኢትዮጵያውያን ክብር ናት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ አሁን የፖለቲካ እና የዘር አጀንዳችን መጠቀሚያ እያደረግናት ነው ብለዋል።

የፕሮቴስታንት አምነት ተከታዮች የኦሮቶዶክስ ሀይማኖትን ማክበር እና መውደድ የምርጫ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ግዴታችሁም ነው ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።ቤተክርሲያኗ በኢትዮጵያ ውስጥ ትልቅ አሻራ ማስቀመጧን በማንሳት፥ ቤተክርስቲያኗ ከእነ ክብሯ እንድትቀጥል እንፈልጋለን ብለዋል።

ሲያጠቃልሉም መልካም ወጣቶችም ሆኑ የፕሮጀክቱ አስተባባሪ አገልጋይ ዮናታን አክሉሉ ካሉበት የከፍታ ስፍራ እንዳይለቁ አሳስበዋል።የመልካም ወጣት ማዕከል ግንባታ ሀሳብ እንዳስደሰታቸው የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ በቅርቡ ኬሔስያን የሰላም ሽልማት ያገኙትን 25 ሺህ ዩሮ ለማዕከሉ ግንባታ እንዲውል አበርክተዋል።

የኢፌደሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በበኩላቸው እንዲህ ዓይነቱ በራስ ተነሳሽነት የነገን ባለ ተስፋዎች እና የሀገር ሀብት የሆኑትን ወጣቶች በማሰባሰብ ከወራት በላይ በጎ መምከር እና በጎ ማስታጠቅ በፈጣሪም በፅድቅ ትልቅ ቦታ እንዳለው እና ለሀገርም ትልቅ ታሪክ ሰሪነት መሆኑን ተናግረዋል።ሁሉም በየደረጃው በዚህ በመቅናት እና በመመኘት የራሱን ሪክ መስራት አለበት ነው ያሉት።እንዲህ ይቅርታና ፍቅርን የሚያስተምሩ ሺዎች ከተሰለፉ ወደ ሚሊዮኖች አድገን በአጭር ጊዜ ራእያችንን እናሳካለን ብለዋል።2009 ዓመተ ምህረት ላይ በአገልጋይ ዮናታን አክሊሉ የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት በየክረመቱ ሲከናወን ቆይቷል።

#FANA


Report Page