#ETH

#ETH


ሀዋሳ ከተማ ወደ ቀድሞ ሰላሟ እየተመለሰች መሆኑ ተገለጸ!

ሀዋሳ ከተማን ወደ ቀድሞ ሰላሟ እየተመለሰች በመሆኑ የውጭና የሀገር ውስጥ ጎብኝዎች መጥተው በከተማዋ ቆይታ እንዲያደርጉ የተለያዩ በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ የተሰማሩ አካላት ጥሪ አቀረቡ፡፡

ከሀገሪቱ የተውጣጡ የሚዲያ አካላት ከተማዋን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

በሀዋሳ ከተማ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታን አስመልክቶ የፌደራልና የክልል ባህልና ቱሪዝም መስሪያ ቤቶች በጋራ በመሆን ወቅታዊ ሁኔታውን በሀገር አቀፍ ያሉ የሚዲያ ተቋማት መጥተው በከተማዋ ያለውን ሰላማዊ ሁኔታ ተመልክተዋል፡፡

ስለ ሀዋሳ ከተማ ሰላምና የሆቴሎች አገልግሎት አሰጣጥ አስተያየታቸውን ከሰጡ ጎብኝዎች መካከል ከአዲስ አበባ የመጡት አቶ ሚሊዮን ታፈሰ እና ከየመን የመጡት ወይዘሮ ብልቂሳ አብደላ ሀዋሳ ከተማ ከወር በፊት ሰላም እንዳልነበር መስማታቸውንና በአሁኑ ጊዜ ከተማዋ ሰላሟ መመለሱን፤ የሆቴሎች አገልግሎትም ጥሩ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በያዝነው ወር የእንግዶች ፍሰት መሻሻል ቢያሳይም የከተማዋን ትክክለኛ ገጽታ የማሳወቁን ተግባር ግን የሚመለከታቸው አካላት በተገቢው አልተወጡትም ያሉት ደግሞ የሌዊ ሪሶርት ስራ አስኪያጅ አቶ ይበለው አለኸው ናቸው፡፡

የጎዶሊያስ ኢንተርናሽናል ሆቴል ባለቤት አቶ አበራ ላንጋኖ በበኩላቸው አሁን ያለውን ሰላማዊ ሁኔታ ለማስቀጠል የሚመለከታቸው አካላት እንዲሰሩበት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አሁን በከተማዋ ያለውን ሰላም ማስቀጠል ከተቻለ የቱሪስት ፍሰቱም እንደሚጨምር ያላቸውን እምነት የገለጹት የደቡብ ክልል ሆቴሎች ማህበር ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ ደጀኔ ጌታቸው ናቸው፡፡

የደቡብ ክልል ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሰብለጸጋ አየለ እንዳሉት በያዝነው ዓመት ከ274 ሺህ በላይ የውጭ ቱሪስቶች ክልሉን ቢጎበኙትም ከአምናው ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃፀር ቁጥሩ በ49 ሺህ ያህል ቀንሷል፡፡ ከዘርፉ የሚገኘውም ገቢ 15 በመቶ መቀነሱን ጠቅሰው በቀጣይም ይህን ማስተካከል የሚያስችል ስራ አጠናክረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

#SRTA

Report Page