#ETH

#ETH


የሐኪሞችን ምደባ ሙሉ ለሙሉ ማቆሙን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ!

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በ13 የህክምና ሙያ ዘርፎች ትምህርታቸውን በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተከታትለው የሚወጡ ባለሙያዎችን የሐኪሞች እጥረት ባሉባቸው አካባቢዎች ይመድብ ነበር። ይሁን እንጂ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በየጊዜው ምደባ የሚያካሂድባቸው የሙያ ዘርፎችን እየቀነሰ መጥቷል።

ከ13 የህክምና ሙጀያዎችች መካከል ስምንቱን በ2010 ዓ.ም ሲያቆም በአምስት ሙያ ዘርፎች ማለትም ጠቅላላ ሀኪም ፤ ላብራቶሪ ፤ ፋርማሲ ፤ አኒስቴዢያና ሬዲዮ ግራፊ ሙያተኞች እስከ 2011 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ መንግስት የስራ ምደባ ሲያደርግባቸው ቆይቷል፡፡

አሁን ላይ ግን በፌደራል ደረጃ ምደባው እንዲቆም መወሰኑን በጤና ሚንስቴር የሰው ሀብት አስተዳደር ዳሬክተር አቶ ሀብታሙ ደምሴ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤምም ምደባው ሙሉ በሙሉ የቀረበትን ምክኒያት እንዲያስረዱ ጠይቋል፡፡ ዳይሬክተሩ አቶ ሀብታሙ ለጣቢያው እንዳሉት ሙያተኛው ከአስገዳጅ ምደባ ወጥቶ ብዙ አማራጮችን እንዲያገኝ ለማድረግና የሚሰለጥነውን ባለሙያ ከመንግስት አቅም ጋር ለማመጣጠን ነው ብለዋል ፡፡

85% የኢትዮጵያ ህዝብ በገጠር የሚኖር ነው ካልን ሀኪሞችን አለመመደብ አብዛኛው ህዝብ የህክምና አገልግሎት እንዳያገኝ አያደርግም ወይ ብለን ላነሳንላቸው ጥያቄም ጤና ሚንስቴር በማዕከል የሚያደርገውን የስራ ምደባ ቢያቆምም ክልሎች ግልፅ አሰራር ተከትለው ሙያተኛውን ባላቸው በጀት እንዲመድቡ ክትትል እናደርጋለን ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

አሁን ሀኪሞች በጤና ሚንስቴር የማይመደቡ መሆኑን ተከትሎ የትምህርት ማስረጃና የስራ ፍቃድ ሲወስዱ ማሻሻያዎች መደረጋቸውንም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

በተለይም ከዚህ በፊት ወደ 427 ሺህ ይከፍሉት የነበረው አሁን በአማካኝ ወደ 51 ሺህ መቀነሱን ተናግረዋል፡፡ በኢትዮጵያ አሁን ባለው መረጃ መሰረት አንድ ሀኪም 10 ሽህ ታካሚዎችን ያክማል፡፡

Via #ETHIOFM

@tsrgabwolde @tikvahethiopia

Report Page