ETH

ETH

ቲክቫህ ኢትዮጵያ

የኢትዮ ሱዳን ከፍተኛ የፖለቲካ ምክክር መድረክ በመካሄድ ላይ ነው

ለሁለት ቀናት የሚካሄደው የኢትዮ ሱዳን ከፍተኛ የፖለቲካ ምክክር መድረክ ዛሬ የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና የሱዳን የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ክቡር ኦማር በሽር ማኒስ በተገኙበት ተከፍቷል፡፡ 

በመድረኩ በድንበር አካባቢ ያሉ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ መረጃ መለዋወጥና በሁለቱ አገራት በድንበር አካባቢ ዘላቂ ሰላምና ፀጥታን ለማስፈን በትብብር መሰራት ባለባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክሯል፡፡

እንዲሁም በሁለቱ አገራት መካከል ከዚህ ቀደም የተቋቋሙት የተለያዩ የድንበር ኮሚቴዎች እና የትብብር ማዕቀፎችን አጠናክሮ ማስቀጠል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክሯል፡፡ በነገው እለትም በተደረሱ ስምምነቶች ላይ ወደ ተግባር ለመለወጥ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት በመፈራረም እንደሚጠናቀቅ ይጠበቃል።


በዚህ የፖለቲካ ምክክር መድረክ በኢትዮጵያ በኩል የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው፤ ከቡር ጄኔራል አደም መሀመድ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እንዲሁም የመረጃ እና ደህንንት፣ የፌደራል ፖሊስ እና ሌሎች ከፍተኛ የጸጥታና ደህንነት ሃላፊዎች የተገኙ ሲሆን በተመሳሳይ በሱዳን ወገን የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርን ጨምሮ የሱዳን የመከላከያ እና የደህንነት መስሪያ ቤት ሃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

ምንጭ፡- የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃልአቀባይ ጽ/ቤት

Report Page