ETH

ETH

ቲክቫህ ኢትዮጵያ

ከዚህ ቀደም በኮቪድ-19 ምክንያት ትምህርት መቋረጡ ይታወቃል፡፡ ይህንኑም መሰረት በማድረግ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስተር መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡ ባወጣውም መግለጫ የሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች በተለያየ መገናኛ አማራጮች ተጠቅመው ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ የተገለጸ ሲሆን የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ግን በቤታቸው ሆነው እያነበቡ እንዲቆዩና የበሽታው ስርጭት ከቆመ ያለውን የዕረፍት ጊዜ ተጠቅመን በአጭር ጊዜ የገጽ ለገጽ ትምህርቱ እንደሚቀጥልና ያ ካልሆነም ወደ 2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተዘዋውሮ የሚቀጥል መሆኑ በመግለጫው ውስጥ ተካቷል፡፡

ነገር ግን የአ.አ.ዩ ፕሬዘዳንት የሆኑት ፕሮፌሰር ጣሰው ወ/ሃና በሰጡት መግለጫ ደግሞ የሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች እንዳለ ሆኖ በተጨማሪም የማታ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች እና የርቀት የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች በተለያየ መገናኛ አማራጮች ትምህርቱ ሲሰጥ እንደቆየ ገልጸዋል፡፡

ሆኖም ግን ከላይ ፕሮፌሰሩ በሰጡት መግለጫ ላይ እኛን በማታው መርሃ ግብር የመጀመሪያ ዲግሪ የመጨረሻ ዓመት ተመራቂ ተማሪዎችን በብዙ ሁኔታ ያላገናዘበ መግለጫ ሆኖ አግኝተነዋል፡፡

1ኛ ትምህርቱ ከተቋረጠበት ቀን ጀምሮ በተባለው ፕላትፎርም ምንም የተሰጠን ትምህርትም ሆነ ከአስተማሪዎች ጋር የተገናኘንበት ምንም ዓይነት ሁኔታ አልነበረም፡፡በተጨማሪም ከዚህ ቀደም ፕሮፌሰሯ በሰጡት መግለጫ መሰረት ወረርሽኙ ሲቀንስ ወደ ትምህርት ገበታችን እንመለሳለን ወይም ወደ 2013 ዓ.ም ሊዛወር ይችላል በሚል ምንም ዓይነት መዘጋጀት አልነበረንም፡፡

2ኛ በተዘጋጀው ፕላትፎርም ትምህርቱ ቀጠለ እንኳን ቢባል እኛ ተመራቂ ተማሪዎች እንደመሆናችን የመመረቂያ ጽሁፍ ለማዘጋጀት ያለው ሁኔታ በጣም አስቸጋሪ ነው ይኽውም መጠይቅ ለመበተን፣ቃለ መጠይቅ ለማድረግ፣ዳታ ለመሰብሰብ እንዲሁም ከአማካሪዎቻችን እና አብረን ከምንሰራው የቡድን አባላት ጋር ለመገናኘት ያለው ሁኔታ በፍጹም የሚፈቅድ አይደለም፡፡

3ኛ አንዳንድ የትምህርት ዓይነቶች ከአስተማሪ ጋር ግዴታ ገጽ ለገጽ ገላጻ የሚያስፈልጋቸው ከመሆናቸው የተነሳ ትምህርት አሰጣጡን በጣም ከባድ ያደርገዋል ለምሳሌ የአካውንቲንግ ትምህርትን ብንመለከት ቁጥር ነክ እና ካልኩሌሽን የሚበዛበት በመሆኑ የገጽ ለገጽ ትምህርቱን ግዴታ ያደርገዋል

4ኛ ከላይ ፕሮፌሰር ጣሰው ወ/ሃና ፕላትፎርም ተዘጋጅቶ ትምህርት እየተሰጠ ነው ማለታቸው ቢታወስም መምህራኖቻችንን ለማናገር በሞከርንበት ጊዜ መምህራኖቹ ምንም ዓይነት መረጃ እንደሌላቸው ነበር የገለጹት በተጨማሪም እንደተባለው በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ተጠቅመን ትምህርት ይቀጥል ማለት ይህን ማደረግ የማይችል ተማሪ ማለትም አቅሙ የኢንተርኔት ወጪን ለመሸፈን የማይችል፣ስማርት ስልክ የሌለው፣ኔትወርክ የማይሰራበት ቦታ የሆነን ሰውን ግንዛቤ ውስጥ አላስገባም አንዲሁም ዜናውን መምህራኖችን ጨምሮ ዜናውን እስካሁን ያልሰሙ ተማሪዎችም አሉ

ይህ ሁሉ በሆነበት ሁኔታ ትምህርቱ በተቀመጠለት የጊዜ ሠሌዳ ተጠናቆ ሀምሌ 4 ተማሪዎችን እናስመርቃለን ማለትና ያለውን ችግር ሳያገናዝቡ ይህንን መግለጫ ማውጣት ተገቢ አለመሆኑ ታይቶ ከላይ ለመግለጽ የሞከርናቸውን ችግሮች አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጠን እንጠይቃለን፡፡

እንደ እኛ የመፍትሄ ሃሳብ ብለን የምናቀርበው ባለው ሁኔታ እና ካለው የጊዜ እጥረት በተጠቀሰው ጊዜ ለማጠናቀቅ አስቸጋሪ በመሆኑ ከዚህ ቀደም ፕሮፌሰሯ እንደተናገሩት ወረርሽኙ የሚቀንስ ከሆነ ያለውን የዕረፍት ጊዜ ተጠቅመን ለመማር ካልሆነም ወደ 2013 ዓ.ም ቢዛወር የተሻለ ነው እንላለን፡፡

Report Page