ETH

ETH

ቲክቫህ ኢትዮጲያ

''የተከበራቹህ የሀገራችን ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች
እንኳን ታላቁ የኢትዮጰያ ህዳሴ ግድብ የተጀመረበት 9ኛ አመት አደረሳቹህ።

ውድ የኢትዮጰያ ህዝቦች

ታላቁ የኢትዮጰያ ህዳሴ ግድብ ወደኃላ ወደ ማይመለስበት ደረጃ እንዲደርስ የግድቡ ገዥ ሃሳቦች አንግባቹህ ሁለንተናዊ ርብርብ እንዳደረጋቹሁት ሁሉ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት እንዳይበቃ እንቅፋት የሚሆነውን ማናቸውም ጣልቃ ገብነትና የውዥንብር ፈተናዎች አሸንፈን ማለፍ የሚጠበቅብን ፈታኝ ግዜ ላይ ሆነን ነው 9ኛውን አመት እያከበርን ያለነው፡፡

የህዳሴ ግድባችን ስንጀምር ባሰርነው ቃልኪዳን መሰረት የውጭ ብድርና እርዳታ ሳንጠብቅ በህዝባችን ሁለንተናዊ ተሳትፎና በፈጣኑ የኢኮኖሚ እድገታችን በተከታታይ ከተገኘው ሀብት በመጠቀም በራስ አቅም እንዲከናወን ርብርብ ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በነዚያ አመታት የህዳሴ ግድባችን የኢትዮጰያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች የጋራ መግባባት ተምሳሌት በመሆን የፈጠረው የይቻላል መንፈስ በያንዳንዱ ዜጋ የእለት ተእለት እንቅስቃሴና ሀገራዊ የኢኮኖሚ መነቃቃት የራሱ መተክያ የሌለው ድርሻ ነበረው፡፡ በግድቡ ይሳተፉ የነበሩ ሙያተኞች አቅም በመገንባት ረገድም ሁነኛ መሰረት መጣል ጀምሮ እንደነበር የሚታወቅ ነው፡፡ ግድባችን በአባይ ተፋሰስ ቀጣና የቁርቁስ ሳይሆን በፍትሃዊነት ላይ የተመሰረተ የጋራ ጥቅምና አብሮነት ማሳያ እንዲሆን የኢትዪጰያ፣ ሱዳንና ግብፅ የሶስትዮሽ ስምምነት እንዲደረስ በማስቻል የግድቡ አስተማማኝነት በአለም አቀፍ ባለሙያዎች ጭምር ዳግም ተጠንቶ የነበረው ጥርጣሬ መሻገር አስችሎ ነበር፡፡

በዚሁም መሰረት እንደ ሁሉም የኢትዮጰያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ሁሉ የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትና ህዝብ ታላቁ የኢትዮዽያ ህዳሴ ግድብ በታቀደለት እንዲጠናቀቅ የበኩሉን ድርሻና ድጋፍ ለማድረግ ከፍተኛ ተግባራዊ ርብርብ በማካሄድ ሃገራዊ ግዴታው ሲወጣ ቆይቷል፡፡ ሃገራዊ ኣደረጃጀቱ የፈጠረውን እድል በመጠቀም፤የህዳሴ ግድብ በመጀመራችን ምክንያት የተፈጠረው ህዝባዊ መነሳሳት በወሳኝ ሃገራዊ ጉዳዮች ብሄራዊ መግባባት ለመፍጠር፣ በህዳሴ ግድብ የተፈጠረው የይቻላል መንፈስ ለሌሎች የልማት ስራዎች ለመጠቀም፤ የህዝቡ የቁጠባ ባህል እንዲዳብርና ከትጥቅ ትግል ጀምሮ ሲሰራበት የቆየው የተፈጥሮ ሃብት እንክብካቤ ተጠናክሮ እንዲቀጥልም በአረንጓዴ ልማት የተፈጠረ መንፈስ እንዲጠናከርም የራሱ አስተዋፅኦ አድርጓል፡፡

በአጠቃሊይ ህበረተሰቡ ቦንድ በመግዛት፣ በልገሳና በልዩ ልዩ ገቢ ማስገኛ ሁነቶች በመሳተፍ ያበረከተው አስተዋፅአ ከ652 ሚልዮን ብር በላይ ደርሷል፡፡ ህብረተሰቡ አሻራውን በታላቁ የኢትዮጰያ ህዳሴ ግድብ ላይ በማኖር ረገድ በዝቅተኛ ገቢ ላይ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ ልቆ መታየት ህዝባችን እንደ ሁሉም ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ሁሉ ቃልኪዳኑን ጠብቆ መዝለቁ ነው፡፡

በህዳሴ ግድባችን እንደማንኛውም ፕሮጀክት የታዩ ጉድለቶችና ክፍተቶች ተለይተው እየተስተካሉ እንዲቀጥሉ ተወስኖ እንቅስቃሴ በተጀመረበት ወቅት በተለይም ከሁለት አመታት ጀምሮ በግድቡ ላይ ከውስጥና ከውጭ ሃይሎች በተነዛ ውዥንብር በታላቁ የኢትዮጰያ ህዳሴ ግድብ ላይ የነበረው ከፍተኛ እንቅስቃሴ መቀዛቀዝ አሳይቷል፡፡

ይሁንና በራስ አቅም ለመገንባት ቃል ኪዳን አስረን የጀመርነው የህዳሴ ግድባችን ከይቻላል መንፈስ ወደ አንችልም ወደሚለው ሃላቀር አስተሳሰብ ወደ ሃላ ተመልሶ ለውጭ ተቋማት ተላልፎ መሰጠቱ በድርድር ሂደት የውጭ አካላት ጣልቃ ገብነት ይበልጥ እንዲጋለጥ አድርጎታል፡፡

ስለሆነም መላ የኢትዮጰያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ታላቁ የኢትዮጰያ ህዳሴ ግድብ ወደሃላ ወደማይመለስበት ደረጃ እንዲደርስ እንደተረባረባቹሁት ሁሉ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት እንዳይበቃ እንቅፋት የሚሆነውን ማናቸውም ጣልቃ ገብነትና የውዥንብር ፈተናዎች በጋራ አሸንፈን ለመሻገር በትግራይ ህዝብና መንግስት እንደ ሁል ግዜ ሁሉ ዝግጁ መሆናቸውን ልገልፅላቹህ እወዳሎህ ፡፡''

ምንጭ፡- የትግራይ ክልል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ

Report Page