ETH

ETH

ቲክቫህ ኢትዮጲያ

የነዳጅ አቅርቦት እጥረት እንደሌለ ተገለፀ

ሀገራዊ የገበያ ማረጋጋት ግብረ-ኃይል መደበኛ ሳምንታዊ የገበያ ማረጋጋት ሥራ አፈጻጸም በገመገመበት ወቅት በአዲስ አበባ የተስተዋለው የነዳጅ ሰልፍ በኮሮና ወረርሽኝ ክስተት የነዳጅ አቅርቦት ይቋረጣል ብሎ በመስጋቱ ምክንያት ነዳጅን ቀድቶ ለማስቀመጥ በመፈለግና አንዳንድ ማደያዎች ሙሉ ነዳጅ እያላቸው ነዳጅ የለንም በሚል የተፈጠረ እንጂ መንግስት የነዳጅ አቅርቦቱን እንደ ከዚህ ቀደሙ ያለ ምንም መቆራረጥ ወደ ሀገር እያስገባ መሆኑን ተገልጿል፡፡

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይክተር አቶ ወንድሙ ፍላቴ እንደተናገሩት ነዳጅን የሚጠቀሙ የህብረተሰብ ክፍሎች በነዳጅ ላይ የሚፈጠር ምንም አይነት እጥረት አለመኖሩን ከግምት ውስጥ በማስገባት ህብረተሰቡ ከአላስፈላጊ ውጥረት ነጻ እንዲሆንና  በማደያዎች አካባቢ መሰለፍ እንደሌለባቸው አስገንዝበዋል፡፡ 

የስርጭት ችግር ቢኖርም ከዚህ ቀደም ይቀርብ የነበረው ናፍጣ  ሙሉ በሙሉ እየቀረበ ሲሆን በቤንዚን አቅርቦት ላይ የተፈጠረው ችግር በዚህ ሳምንት ውስጥ በፍጥነት ይፈታል፡፡

ነዳጅን በህገወጥ መንገድ በጀሪካና በበርሜል በመቅዳት በሚያዘዋውሩ ግለሰቦችና የማደያ ባለቤቶች ላይ መንግስት አስፈላጊውን ክትትልና ቁጥጥር በማረድግ ህግን የማስከበር ስራ የሚሰራ መሆኑን የግብረ ኃይሉን ሪፖርት ውይይት የተከታተሉት የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተሩ አቶ ወንድሙ ገልፀዋል፡፡

Report Page