#ETH

#ETH


የግል መገልገያ እቃዎችን ወደ ሀገር ለማስገባት የሚያስፈልጉ ማስረጃዎች ምን ምን ናቸው?

ተመላሽ ኢትዮጵያዊ፡-

- በውጭ አገር የቆየበትን ጊዜ እና ጠቅሎ ወደ ኢትዮጵያ መመለሱን የሚገልጽ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ (Authenticated) የመሸኛ ደብዳቤ ከነበረበት አገር ካለው ወይም የነበረበትን ሀገር ጭምር ከሚያገለግለው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ወይም ቆንስላ ወይም ሚስዮን ማቅረብ ያስፈልጋል፤

- የኢትዮጵያ ሚስዮን ከሌለበት አገር የሚመጣ ከሆነ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የመኖሪያ ፈቃዱን እና የስራ ውሉን ሳያሰርዝ የመጣ መሆኑን በማጣራት በፓስፖርቱ ላይ በተለጠፈው ስቲከር ላይ ተሰርዟል (Void) የሚል ማህተም በማድረግ የሚሰጠውን የመሸኛ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል፤ 

ከስደት ተመላሽ፡-

- በስደት ከቆየበት አገር ካለው ወይም በስደት የቆየበትን ሀገር ጭምር ከሚያገለግለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ወይም ሚስዮን የተሰጠውን መሸኛ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል አረጋግጦ ማቅረብ አለበት፤

- የኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ ቆንስላ ወይም ሚስዮን ከሌለበት ሀገር የሚመጣ ከሆነ ከደህንነት፣ ኢሚግሬሽንና የስደተኞች ጉዳይ ባለስልጣን ከስደት ተመላሽ መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ማቅረብ አለበት፤

- በስደተኛነት ቆይቶ በላኪው ሀገር እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል በሚደረግ ስምምነት መሰረት ወደ ኢትዮጵያ የሚመለስ ከስደት ተመላሽ ከደህንነት፣ ኢሚግሬሽንና የስደተኞች ጉዳይ ባለስልጣን ከስደት ተመላሽ መሆኑን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ ማቅረብ አለበት፡፡

ባለሀብት፡

- ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት ያደረገ ባለሀብት መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ከሚመለከተው የኢንቨስትመንት ኮሚሽን/ ቢሮ ማቅረብ፤

አግባብ ካለው የመንግስት መ/ቤት ወይም ተቋም ጋር በተደረገ ስምምነት በኢትዮጵያ ለማገልገል የሚመጣ ባለሙያ፡-

- በኢትዮጵያ ለማገልገል የሚመጣ የውጪ አገር ነዋሪ ኢትዮጵያዊ፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊ ወይም የውጪ ሀገር ዜጋ ባለሙያ ስምምነቱን ባደረገው የመንግስት መ/ቤት ወይም ተቋም የበላይ ሃላፊ የተፈረመ ደብዳቤ ማቅረብ አለበት፤

መንግስት በሚያደርገው ልዩ ጥሪ የሚመጣ፡-

- መንግስት በሚያደርገው ልዩ ጥሪ መሰረት በኢትዮጵያ ለማገልገል የሚመጣ የውጪ ሀገር ነዋሪ፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊ እና የውጪ ሀገር ዜጋ ባለሙያ በጥሪው መሰረት ኢትዮጵያን ለማገልገል መምጣቱን የሚያስረዳ ከነበረበት አገር ካለው ወይም የመጣበትን ሀገር ጭምር ከሚያገለግለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ወይም ሚስዮን የተሰጠ እና በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ (Authenticated) ደብዳቤ ማቅረብ አለበት፡፡

በግል ሥራ፣ በቅጥር ወይም በትምህርት ቆይቶ የሚመጣ፡-

- በግል ስራ፣ በቅጥር ወይም በትምህርት ውጪ ሀገር ቆይቶ የሚመለስ ኢትዮጵያዊ ከመጣበት አገር ካለው ወይም የመጣበትን ሀገር ጭምር ከሚያገለግለው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ወይም ሚስዮን የተሰጠ በዚሁ ሀገር ውስጥ በግል ስራ፣ በቅጥር ወይም በትምህርት የቆየ መሆኑን የሚያስረዳ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ ደብዳቤ ማቅረብ አለበት፡፡

Report Page