#ETH

#ETH


#NEW

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ በ 0 አመት አዲስ ቅጥር የ2010 እና 2011 ዓ.ም በተለያዩ የመንግስትና የግል ዩንቨርሲቲ በመጀመሪያ ድግሪ የተመረቃችሁ የተወዳደራችሁ እና ፈተና ከወሰዳችሁ ውስጥ በኮድ አፃፃፍ ስህተት እና በሌሎችም ቅሬታ ያቀረቡና ያላቀረቡትንም ጨምሮ ለየካቲት 16 ቀን 2012 ዓ.ም ምላሽ እንደምንሰጥ በማስታወቂያ መለጠፋችን ይታወቃል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

1. በኮድ (ID) ስህተት ምክንያት ውጤታቸው የተሰረዘ ቅሬታ ያቀረቡም ሆነ ያላቀረቡ በሙሉ የማጣራት ስራ የተሰራ በመሆኑ ፤

2. ከማለፊያ ነጥብ በላይ የሆኑ waiting በተጠባባቂ የሚመደቡ የሚል የሚያሳይ መሆኑ፤

3. ከማለፊያ ነጥብ በታች የሆኑ Failed የሚል የሚያሳይ መሆኑ፤

4. በ Waiting List ውስጥ በየትምህርት ዓይነቶች እና እንደውጤታቸሁ ቅደም ተከተል በቀጣይ ተቋማት ክፍት መደብ በሚልኩልን ጊዜ እስከ ስድስት ወራት ብቻ በሁለተኛው ዙር ምደባ የምናደርግ ይሆናል፤ ቀደም ሲል የምንጠቀምበት በነበረው ዌብ ሳይታችን www.addis.gov.et ላይ ከየካቲት 23/2012 ዓ.ም ጀምሮ መመልከት የምትችሉ ሲሆን በትዕግስት እንድትጠባበቁ እየገለፅን፡፡ ከዚህ ውጪ ምንም ዓይነት ቅሬታ የማንቀበል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

[የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ]

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia


Report Page