#ETH

#ETH


ቋሚ ኮሚቴው በስራ ላይ ያለው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ለረጅም ጊዜ በስራ ላይ የቆየ በመሆኑ እና የማምረቻ ወጪን መሰረት አድርጎ የሚሰላ በመሆኑ ግልፅነት የሚጎድለው ነው። ይህን ለማስቀረትም አዲሱ አዋጅ በመሸጫ ዋጋ ላይ እንዲሰላ በማድረግ ለከፋይ እና አስከፋዩ ግልፅነት የሚፈጥር ይሆናል።

በተጨማሪም ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች በአካባቢ ደህንነት ላይ እያስከተሉት ያለው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ከተወሰነ ዓመት በላይ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡ ለመገደብ እንዲሁም ለጤና ጎጂ በሆኑ ምርቶች ላይ ያለውን የኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔን በመፈተሽ ማስተካከል አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ አዋጁ ተዘጋጅቷል።

በረቂቅ አዋጁ ላይ በተደረጉ ማሻሻያዎች  ፦

- ከ1 ሺህ 300 ሲሲ ያልበለጠ የፈረስ ጉልበት ያላቸው ተሽካረካሪዎች እና ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች ላይ ተጥሎ የነበረው ኤክሳይዝ ታክስ አዲስ በሀገር ውስጥ የሚገጣጠሙ፣ ሙሉ በሙሉ ተበትነው የቀረቡ፣ በሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪ እንዲገጣጠሙ በከፊል ተበትነው የገቡ እና አዲስ ሙሉ በሙሉ ተገጣጥመው የቀረቡ ላይ እንዲጣል የሚጠይቀው የኤክሳይዝ ታክስ ከ30 በመቶ ወደ 5 በመቶ ዝቅ እንዲል ማሻሻያ ተደርጎበታል።

- ከ1 ዓመት እስከ ከ2 ዓመት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ላይ እንዲጣል የሚጠይቀው የኤክሳይዝ ታክስ ከ80 በመቶ ወደ 55 በመቶ እንዲሁም፥ ከ2 ዓመት እስከ ከ4 ዓመት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ላይ እንዲጣል የሚጠይቀው የኤክሳይዝ ታክስ ከ130 በመቶ ወደ 105 በመቶ ዝቅ እንዲል ማሻሻያ ተደርጎበታል።

- ከ4 እስከ 7 ዓመት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ላይ እንዲጣል የሚጠይቀው የኤክሳይዝ ታክስ ከ230 በመቶ ወደ 205 በመቶ ዝቅ እንዲል ማሻሻያ ተደርጓል።

- ከ7 ዓመት በላይ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ላይ እንዲጣል የሚጠይቀው የኤክሳይዝ ታክስ ከ430 በመቶ ወደ 405 በመቶ ዝቅ እንዲል ማሻሻያ ተዳርጓል።

- በሲጋራ ላይ የተጣለው የኤክሳይዝ ታክስ ምጣኔ በፓኬት በዋጋው 30 በመቶ እንዲሁም በፍሬ 5 ብር የነበረው በኤክሳይዝ ታክስ ማሻሻያው ተጨምሮ 8 ብር እንዲሆን ተደርጓል።

- በረቂቅ አዋጁ የታሸገ ውሃ ላይ ተጥሎ የነበረው ኤክሳይዝ ታክስ ከ15 በመቶ ወደ 10 በመቶ ዝቅ እንዲል ተደርጓል።

- በቴሌኮም አገልግሎቶች ላይ እንዲጣል በኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጁ ቀርቦ የነበረው የ5 በመቶ ኤክሳይዝ ታክስ እንዲወጣ ተደርጓል።

- አዋጁ በማሻሻያው ከፀናበት እለት በፊት የባንክ ፍቃድ የተሰጣቸው እና አዋጁ ስራ ላይ ከዋለበት እለት አንስቶ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገር በሚገቡ እቃዎች ላይ ኤክሳይዝ ታክስ የሚጣለው እና የሚሰበሰበው፥ በኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ ቁጥር 307/1995 በተሻሻለው ድንጋጌዎች መሰረት ይሆናል። ይህም በአዲሱ ማስተናገድ በታክስ አስተዳደር ስርዓት ላይ ችግር ስለሚያስቀምጥ ገደብ ተቀምጧል።

- ከቅጣት ጋር ተያይዞ በረቂቅ አዋጁ ላይ የተቀመጠው ድንጋጌ ዝቅተኛውን የቅጣት ገደብ የማያስቀምጥ በመሆኑ አንቀጹ ጥፋተኛ ሆኖ የተገኘ ሰው ከ3 ዓመት እስከ 5 ዓመት የእስር ቅጣት እና ከ50 ሺህ እስከ 100 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት እንዲጣል በሚል ማሻሻያ ተደርጎበታል።

[FBC]

Report Page