#ETH

#ETH


ሀገር ዓቀፍ መረጃ፦

• በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ በኖቭል ኮሮና ቫይረስ በሽታ መያዙ የተረጋገጠም ሆነ በለይቶ ማቆያ ማዕከሉ ሆኖ ክትትል የሚደረግለት ሰው የለም።

• የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኖቭል ኮሮና ቫይረስ የላቦራቶሪ ምርመራ እዚሁ በተቋሙ ማድረግ የጀመረ በመሆኑ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊላክ የነበረ የ3 ሰዎች ናሙና ምርመራ በማድረግ ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸውን ማረጋገጥ ችሏል፡፡ በተጨማሪም የ3ቱ ወደ ደቡብ አፍሪካ ተልከው የነበሩ ናሙናዎች ውጤት የደረሰን ሲሆን ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸዉ ተረጋግጧል፡፡

• የኖቭል ኮሮና ቫይረስን በሽታ የመከላከል ዝግጁነትን ለማጠናከር ኢንስቲትዩቱ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በአዲስ አበባ ለሚገኙ 13 ሆስፒታሎች የተለያዩ ግብዓቶችን አሰራጭቷል፤እንዲሁም ለክልል ሆሲፒታሎች ለማሰራጨት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀዋል፡፡

• የቫይረሱን ስርጭት አስመልክቶ እስከ አሁን ድረስ 31 ጥቆማዎች ለኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል (Emergency Operation Center) ደርሰው ማጣራት ተደርጎባቸዋል፣ ከነዚህ ውስጥ 14ቱ በልየታ ቆይተው ናሙናቸው ተመርምሮ ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸው በመረጋገጡ ከለይቶ ማቆያ ማዕከሉ እንዲወጡ ተደርጓል፡፡

• የበሽታውን ልየታ ስራ ለማጠናከር የልየታ ቡድኑን ለሚቀላቀሉ የጤና ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

• በሐዋሳ ቫይረሱን የመከላከል ዝግጁነትን ለመደገፍ ቡድን ተልኳል፡፡

• በምክትል ጠቅላይ ሚኒስተር ክቡር አቶ ደመቀ መኮንን የሚመራው ብሔራዊ ግብረ ሃይል ጥር 29/2012 ስብሰባ አካሂዷል፡፡

• ለሆቴሎች፣ ታክሲ ሾፌሮች እና ለመገናኛ ብዙሀን ባለሙያዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለመስጠት ዝግጅቶች ተጠናቀዋል፡፡

@tikvahethiopia


Report Page