ETH

ETH

ቲክቫህ ኢትዮጲያ

ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ-ካርታ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ ጥናት እየተደረገበት እንደነበር ጠቅሶ ጥናቱን በቡድን ሲመሩ ለነበሩና ምርምሩን ሲያደርጉ ለነበሩ አርባ ያህል ለሚጠጉ መሪ ተመራማሪዎችና ተመራማሪዎች  ዕውቅና ሰጥቷል፡፡

የቀድሞ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር የሆኑት ክቡር ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ እንደተናገሩት በ2008 ዓ.ም የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ-ካርታ ጥናት እንዲደረግ ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ጋር የአገሪቱን የትምህርት ችግር መፍታት እንዲችል የታቀደ መሆኑን አንስተው የስትሪም ኮሚቴ በማቋቋምም ጥናቱ በመሪ ተመራማሪዎች እንዲካሄድ መደረጉን ገልፀዋል፡፡ 

ዶ/ር ጥላዬ አያይዘውም በዚህ ታሪካዊ ስራ ላይ ተሳትፈው አሁን የተደረሰበትን ውጤት ለትግበራ እንዲበቃ ሌት ተቀን ሲሰሩ የቆዩትን ተመራማሪዎች እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋቸዋል፡፡

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር የሆኑት ክብርት ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማርያም በበኩላቸው ይህንን ትልቅ አገራዊ አጀንዳ ለማስፈፀም ዶ/ር ጥላዬ ጌቴ ሌት ተቀን ያደረጉትን አድካሚ ትጋት በምስጋና አድንቀው፣ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ-ካርታ ጥናት የማይነካው፣ የማይዳስሰው ጉዳይ የሌለ ከመሆኑም በተጨማሪ የመፍትሄ ምክረ-ሃሳብ የሚያመላክት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

ሚኒስትሯ አያይዘውም ትምህርትና ስልጠና ማለት ትውልድን ማስቀጠል፣ ትውልድን ማስቀጠል ማለት ደግሞ አገርን ማስቀጠል ስለሆነ የዚህ ታሪክ አካል መሆን ዕድለኛ መሆን እንደሆነ አስቀምጠዋል፡፡ 

( የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት )

Report Page