#ET

#ET


#update የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት መማክርት ጉባኤ በትምህርት ዘርፍ የሚነሱ ችግሮችን ለመፍታት አስተዋጽኦው የጎላ መሆኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታው ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ ተናገሩ።

የመማክርቱ አባላት ካላቸው ልምድ አንጻር ዘርፉን ይደግፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም ነው ሚኒስትር ዲኤታው የተናገሩት። ከዚህ ባለፈም ጉባኤው ተበታትኖ ያለውን የምሁራንን አቅም ወደ አንድ መድረክ ለማምጣት ወሳኝ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ብሎም ውጤታማ የጥናትና ምርምር ስራዎችን ተግባራዊ ለማድረግም፥ መማክርቱ በቀጣይ የሚያከናውናቸው ተግባራት እንዳሉም ጠቁመዋል። 

የመማክርቱ አባላት በበኩላቸው የትምህርት ጥራት ላይ የሚነሱ ጥያቄዎችን ለመፍታት እና ዘርፉን በቀጣይ ውጤታማ ለማድረግ የበኩላቸውን ለማበርከት መዘጋጀታቸውን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከስምንት ወራት በፊት ያቋቋመው የመማክርት ጉባኤ በሃገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ ምሁራንን ያካተተ ነው።

አባላቱ እንደየ ዝንባሌያቸው ሃገራቸውን ለማገልገል ያስችላቸው ዘንድ በተለያዮ የስራ መስኮች ተከፋፍለው እየተንቀሳቀሱም ይገኛሉ፡፡

Via #EPA

@tsegabwolde @tikvahethiopia

Report Page