#ET

#ET


ከመጪው ዓመት ጀምሮ የአስረኛ ክፍል አጠቃላይ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና እንደሚቀር የትምህርት ምኒስትሩ ዶክተር ጥላዬ ጌጤ ተናገሩ። 

በአዲሱ የኢትዮጵያ የትምህርት ፍኖተ-ካርታ መሠረት ከሚቀጥለው አመት ጀምሮ ተግባራዊ በሚሆነው አሰራር ለስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች ክልላዊ ፈተና ይሰጣል ተብሏል። የትምህርት ምኒስትሩ ዶክተር ጥላዬ በዛሬው ዕለት በትምህርት ፍኖተ-ካርታ ላይ ረዘም ያለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።ምኒስትሩ አጠቃላይ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ተብሎ የሚጠራው እና አስረኛ ክፍልን ለሚያጠናቅቁ ተማሪዎች ይሰጥ የነበረው አገር አቀፍ ፈተና ከሚቀጥለው አመት ጀምሮ እንደማይኖር መናገራቸውን የዶይቼ ቬለ ዘግቧል።

ከ1993 ዓ.ም. ጀምሮ ይሰጥ በነበረው አጠቃላይ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና በአብዛኛው ተማሪዎች ዘጠኝ የትምህርት አይነቶች ሲፈተኑ ቆይተዋል። በሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ አማካኝነት የሚሰጠውን ይኸን ፈተና ያለፉ ተማሪዎች ለተጨማሪ ሁለት አመታት ወደ መሰናዶ ትምህርት ይሻገራሉ።በኢትዮጵያ የትምህርትና ሥልጠና ሥርዓት አወቃቀር ላይ በሚደረገው ለውጥ ከ1ኛ-6ኛ ክፍል የአንደኛ ደረጃ፤ 7ኛ እና 8ኛ ክፍል መለስተኛ እንዲሁም ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ይሰጣል።

በዚህም መሠረት መጀመሪያ ደረጃ አንደኛ ሳይክል (ከ1ኛ ክፍል እስከ 4ኛ ክፍል)፤ መጀመሪያ ደረጃ ሁለተኛ ሳይክል (ከ5ኛ እስከ 8ኛ ክፍል)፤ ሁለተኛ ደረጃ አንደኛ ሳይክል (9ኛ እና 10ኛ ክፍል) እና ሁለተኛ ደረጃ መሰናዶ ትምህርት (11ኛ እና 12ኛ ክፍል) ተብሎ ሥራ ላይ የነበረው አወቃቀር ይቀየራል።በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት በክልላዊ መንግሥታት የሚሰጥ የስድስተኛ ክፍል ፈተና እንደሚኖር ምኒስትሩ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የትምህርት ሥርዓት «መጀመሪያ ደረጃ ሁለተኛ ሳይክል» ተብሎ በሚጠራው ምዕራፍ መጨረሻ ለ8ኛ ክፍል ተማሪዎች በክልሎች የሚሰጠው የሚሰጠው ፈተና ሀገር አቀፍ ይሆናል ተብሏል።

©DW 

Report Page