#et

#et


ዩኒቨርሲቲዎች የፌዴራል ተቋምነታቸው ሊረጋገጥ፤ የአካዳሚክ ነጻነታቸውም ሊከበር ይገባል!

አሁን ባለው ሁኔታ ዩኒቨርሲቲዎች የሚስተዋለው እንደ ፌዴራል ሳይሆን እንደ አንድ አከባቢ ተቋም የመንቀሳቀስ አዝማሚያ ፈር ሊበጅለትና የፌዴራል ተቋምነታቸው ሊረጋገጥ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡ የአካዳሚክ ነጻነታቸው ተከብሮ እንዲሰሩ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ተጠቁሟል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ተቋምም ምልከታው ተገቢና ሊታረም እንደሚገባው በመጠቆም፤ ዩኒቨርሲቲዎች የፌዴራል ተቋም ሆነው እንዲሰሩ እንደሚደረግና የአካዳሚክ ነጻነታቸው እንዲከበር የሚያስችሉ እርምጃዎችም እንደሚወሰድ አረግግጧል፡፡

በ2012 የትምህርት ዘመን ወደትግበራ የሚገባውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ አስመልክቶ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴት አዘጋጅነት ዛሬ በሸራተን አዲስ በተካሄደው የባለድርሻዎች የውይይት መድረክ ላይ እንደተገለጸው፤ ዩኒቨርሲቲዎች በአደረጃጀታቸውም ሆነ በአሰራራቸው የፌዴራል ሳይሆን የአከባቢ ተቋማት መስለዋል፡፡

ከተማሪዎች ምደባ እስከ መምህራንና አስተዳደር አካላት ያለው እውነትም ይሄንኑ ያሳያል፡፡ ይህ ደግሞ በዩኒቨርሲቲዎች ለሚስተዋለው አለመረጋጋት ጭምር ምክንያት ስለሚሆን ሊታረም፤ ዩኒቨርሲቲዎችም የፌዴራል ተቋምነታቸው ሊረጋገጥ ይገባዋል፤ ሲሉ ተሳታፊዎች ጠይቀዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች የአካዳሚክ ነጻነታቸው ሊከበርና ተልዕኳቸውን መፈጸም ላይ ሊያተኩሩ የሚችሉበት እድል ሊሰጣቸው እንደሚገባም ነው ተሳታፊዎቹ ያሳሰቡት፡፡ ለዚህ ደግሞ ዩኒቨርሲቲዎች ከፖለቲካ ተጽዕኖ እንዲላቀቁ ማድረግ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

ሚኒስቴሩ በበኩሉ፣ የተባለው ነገር እውነት መሆኑን በመጠቆም፤ ከተማሪዎች ምደባ ጀምሮ ዩኒቨርሲቲዎች የፌዴራል ተቋም እንዲሆኑ የሚያስችል እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግሯል፡፡ ነጻነታቸውን ከማረጋገጥ አኳያም በዩኒቨርሲቲዎች ያሉ የፖለቲካ አደረጃጀቶች እንዲወጡ፤ በተለይም አራቱ ድርጅቶች በዩኒቨርሲቲዎች ያላቸው አሰራር እንዲወገድ የሚደረግ መሆኑን አረጋግጧል፡፡

#EPA

Report Page