#ET

#ET


NEW YEAR NEW THINKING!

Launching Reform Initiatives in Higher Education

በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የለውጥ ስራዎችን ማስጀመሪያ ውይይት መድረክ!

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በአገራችን የመጀመሪያውን የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታ ከሶስት ዓመታት በላይ ከፈጀ የዝግጅት ምዕራፍ በኃላ ከ2012 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡ ይህ ፍኖተ ካርታ አጥኚ ቡድን ተቋቁሞ የትምህርትና ስልጠና ስርዓቱ ያለበትን ሁኔታ ከፈተሸ ወዲያ የደረሰባቸውን ችግሮች ሊቀርፉ የሚችሉ የመፍትሄ ሃሳቦች የተካተቱበት ነው፡፡ ፍኖተ ካርታው እስከ 2022 ዓ.ም ድረስ የሚተገበር ሲሆን 2012 ዓ.ምም የመጀመሪያው የትግበራ ዓመት ይሆናል፡፡ ፍኖተ ካርታው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያሉ ችግሮችን ለይቶ መፍትሔዎችን አስቀምጧል፡፡

በፍኖተ ካርታ ዝግጅት ወቅት የተለዩ ችግሮች

•የሥርዓተ ትምህርት አዘገጃጀት ይዘትና ትግበራ ችግር

• የዩኒቨርስቲዎችዎች በተልዕኮ አለመለየት

• የትምህርት አደረጃጀት ችግር

• የህጎች፣ የአሠራሮችና ስታንደርዶች አለመኖርና አለመናበብ

• በቂና ብቁ የሰው ኃይልና የቁሳቁስ ግብዓቶች ከትምህርት መስፋፋቱ ጋር አለመጣጣም

• ዩኒቨርስቲ-ኢንዱስትሪ ትስስር ዝቅተኛ መሆን/አለመኖር

• የሲቪል ሰርቪሱ አለመዘመን - ሥልጠና መስክና የሥራ ገበያ አለመጣጠም

ሲሆኑ በዚህ ምክንያት የመጡ ችግሮች ደግሞ የሚከተሉት ናቸው፡፡

• የስነምግባር እና የሞራል ውድቀት

• ስርዓት አልበኝነትና ምክንያታዊ ያለመሆን

• የስራ ጠባቂነትና ጥገኝነት

• የወቅታዊ አገራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮችን ያለማወቅና ያለመረዳት

• የተግባቦትና የመረዳዳት ችግር

• ዘመኑ የደረሰበት የቴክኖሎጂ እውቀትና ክህሎት ይዞ አለመገኘት

በፍኖተ ካርታው እነዚህን ችግሮች ከስር መሰረታቸው ለመቅረፍ የሚያስችሉ የመፍትሄ ምክረ-ሃሳቦች

ተቀምጠዋል፡፡ ዋና ዋናዎቹም ፡-

• የአንደኛ አመት ተማሪዎችን የታሪክ፣ የጂኦግራፊና አንትሮፖሎጂ፣የኮምፒዩቴሽናል ክህሎት፣ የስነምግባር፣ የቋንቋ፣ የስነተግባቦት፣ ምክንያታዊነት፣ ፣የቴክኖሊጂ እና ዓለም ዓቀፋዊ ዕዉቀት ሊያስጨብጡ የሚችሉ ኮርሶችን መስጠት

• ዩኒቨርስቲዎች እንደተልኳቸው ትኩረት ማደራጀት፤ የምርምር፣ የአኘላይድ ሳይንስ፣ የቴክኒካል ዩኒቨርስቲ ሆነው እንዲደራጁ ማድረግ፣

• የዩኒቨርስቲ ትምህርት ቆይታ 4 አመት እንዲሆን (ለኢንጂነሪንግ 5፤ ለሜዲሲን 6)፣ 2 አመት Masters, 4 ዓመት Ph.D.,

በዚሁ ግኝት መሰረት ከ2012 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ለሁሉም ተማሪዎች በመጀመሪያ ዓመት የሚሰጡ 15 የትምህርት አይነቶች የተለዩ ሲሆን እነዚህም ፡-

1. Critical Thinking

2. General Psychology

3. Global Trends

4. Economics

5. Communicative English Language Skills I

6. Geography Of Ethiopia And The Horn

7. Mathematics (For Natural Science/ For Social Sciences)

8. Introduction To Emerging Technology

9. Anthropology

10. Entrepreneurship

11. History Of Ethiopia And The Horn

12. Communicative English Language II

13. Moral And Civics Education

14. Inclusiveness

15. Physical Fitness

ዩኒቨርስቲዎችን በተልዕኮ የመለየት ስራዎችም ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናሉ፡፡ በተልዕኮ መለየት ሲባል ለምሳሌ በሁሉም ዩኒቨርስቲዎች ኢንጂነሪንግ ትምህርቶች የሚሰጡ ከሆነ በቀጣይ የተሻለ ልምድና የማስተማሪያ ግብዓቶች ያሟላው ዩኒቨርስቲ ብቻ እንዲያስተምረው ይሆናል ማለት ነው፡፡ ይሄ ስራ ጊዜ የሚፈልግ ስለሆነ በአንድ ጊዜ ሊገባበት ባይችልም ዩኒቨርስቲዎቹ ያሉበትን ደረጃ በመፈተሸ የትኛው ተልዕኮ እንደሚሰጣቸው የማሳወቅ ስራዎች ይሰራሉ፡፡ በሂደት ደግሞ ሙሉ ለሙሉ ወደተሰጣቸው ተልዕኮ ብቻ አተኩረው ይሰራሉ፡፡ ይሔም የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ አንዱ መፍትሔ ይሆናል፡፡


Report Page