#ET

#ET


የመሬት መንሸራተት፣ የወንዞች ሙላትና ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊከሰት ይችላል!

*****************************************ቀጣይ አንድ ሳምንት ውስጥ በአብዛኛው የአባይ፣ የተከዜ፣ የባሮ ኦኮቦ፣ የኦሞ ጊቤ፣ የላይኛውና መካከለኛው ስምጥ ሸለቆ፣ የአዋሽ የላይኛውና ዋቢ ሸበሌ ተፋሰሶች፤ የላይኛውና መካከለኛው ዋቢ ሸበሌ፤ የላይኛው አፋር ደንከል፤ ገናሌ ዳዋ፣ ኦጋዴን እንዲሁም ታችኛው አዋሽና ስምጥ ሸለቆ አካባቢ የመሬት መንሸራተት፣ የወንዞች ሙላትና ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊከሰት ስለሚችል ጥንቃቄና ክትትል እንደሚያስፈልግ ብሄራዊ የሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ።

ኤጀንሲው እንዳስታወቀው ከነሃሴ 5/ 2011 እስከ ነሃሴ 14 /2011 ዓ.ም ከላይ በተጠቀሱት ስምጥ ሸለቆዎች፣ ተፋሰሶች አልፎ አልፎ ከባድ ዝናብ ሊኖር እንደሚችል እንዲሁም መጠነኛ እርጥበት እንደሚኖራቸው ትንበያው ይጠቁማል።

ከከፍተኛ እርጥበት እስከ መጠነኛ እርጥበት የሚኖርባቸው ተፋሰሶች ላይ የሚከሰተው ዝናብ በገደላማ ቦታዎች ላይ የመሬት መንሸራተት፤ የወንዞችና የውሃ ማጠራቀሚያዎች መሙላት እንዲሁም ለጎርፍ ተጋላጭ አካባቢዎች ላይ ደግሞ ቅጽበታዊ ጎርፍ ሊከሰት ስለሚችል አስፈላጊውን ጥንቃቄና ክትትል ማድረግ ተገቢ መሆኑን ጠቁሟል።

ኤጀንሲው በመግለጫው አክሎም፤ እስከ ነሃሴ 14 ባሉት ቀናት ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅና ምዕራብ ወለጋ፣ ጂማ፣ ኢሉአባቦራ፣ ሁሉም የሸዋ ዞኖች፣ ምዕራብና ምስራቅ ሀረርጌ፣ አዲስ አበባ፣ ከአማራ ክልል ምዕራብና ምስራቅ ጎጃም ዞኖች፣ የሰሜንና የደቡብ ጎንደር፣ የባህር ዳር ዙሪያ፣ አዊ ዞን፣ የሰሜን ሸዋ በተጨማሪም የደቡብ ወሎ ዞኖች፣ የትግራይ ዞኖች፣ የጋምቤላና ቤኒሻንጉል ዞኖች፤ ከደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል የካፋ፣ የቤንች ማጂ፣ የጉራጌ፣ የሀዲያ፣ የወላይታ፣ የዳውሮ፣ የጋሞጎፋ፣ የሲዳማ ዞኖች መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚኖር አስታውቋል።

በተጨማሪም የአርሲና ባሌ ዞኖች፣ ድሬዳዋና ሀረሪ፣ የአፋር ዞን 3 እና 5 እንዲሁም ጂግጂጋና የሽንሌ ዞኖች በአንዳንድ ስፍራዎቻቸው ላይ በአብዛኛው ከመደበኛው ጋር የተቀራረበ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው የሚጠበቅ ሲሆን የተቀሩት የሀገሪቱ አካባቢዎች ደረቅ ሆነው እንደሚሰነብቱ ትንበያው አመላክቷል።

Via #EPA

Report Page