ER

ER


#AddisAbaba : የፍትህ ሚኒስቴር የህ/ተ/ም/ቤት አሸባሪ ብሎ ለፈረጀው ትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (TPLF) ድጋፍ ያደርጋሉ፤ ግንኙነትም አላቸው ተብለው የታሸጉ ፋብሪካዎች ፣ የተለያዩ ድርጅቶች አስተዳዳሪ ተሹሞላቸው በቅርቡ ስራ ይጀምራሉ ሲል አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ይህን ያሳወቀው ለሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

ከጥቂት ወራት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ በርካታ የንግድ ድርጅቶች እና ሆቴሎች የንግድ ህጉን በመጣስ እና ለTPLF የሽብር ተግባር ድጋፍ ያደርጋሉ በሚል ጥርጣሬ ታሽገው ነበር።

ከተዘጉት የንግድ ድርጅቶች መካከል በርካቶቹ ተመልሰው እንደተከፈቱ ነገር ግን ቁጥራቸው በግልፅ የማይታወቅ ትልልቅ ሆቴሎች ጭምር አሁንም ድረስ ዝግ እንደሆኑ ናቸው።

ከሆቴሎቹ መካከል ፦

- ካሌብ ሆቴል

- ኔክሰስ ሆቴል

- አክሱም ሆቴል

- ንግስተ ሳባ ሆቴል

- ሀርመኒ ሆቴል እና ሌሎችም ይገኙበታል።

ቃላቸውን ለሪፖርተር ጋዜጣ የሰጡት የፍትህ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ፍቃዱ ፀጋ ፥ " በህገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ የነበሩትን የንግስ ድርጅቶች እና ሆቴሎች አስተዳዳሪ ተሹሞላቸው ስራቸውን እንደገና እንዲቀጥሉ ለማድረግ እየተሰራ ነው" ብለዋል። ነገር ግን በድርጅቶቹ ላይ የሚደረገር ምርመራ እንደሚቀጥል ለጋዜጣው አሳውቀዋል።

ፍትህ ሚኒስቴር በወንጀል የተጠረጠሩትን ተቋማትና ግለሰቦች ወደፍርድ እንደሚያቀርብ የጠቀሱት ሚኒስትር ዴኤታው የከተማ አሰተዳደሩ ድርጅቶቹን ለመክፈት ወይም ላለመክፈት አስተዳደራዊና የወንጀል ህጉን መሰረት በማድረግ ውሳኔ እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

አቶ ፈቃዱ ፥ በሆቴሎችም ሆነ በንግድ ድርጅቶች ውቅጥ ይሰሩ የነበሩ ሰራተኞች ስራ አጥ መሆን የለባቸውም ያሉ ሲሆን ድርጅቶቹ በተቻለ መጠን ወደ ስራ እንዲመለሱ ለማድረግ እተሰራ ነው ብለዋል።

በተመሳሳይ ለሕወሓት ድጋፍ ያደርጋሉ የተባሉ ወይም በድርጅቶቹ የበላይ ኃላፊዎች አማካይነት ይዘወራሉ ተብለው የተጠረጠሩ ሕንፃዎች፣ በፍርድ ቤት ውሳኔ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አስተዳዳሪ ሆኖ እያከራያቸው፣ የባንክ ብድር ካለባቸውም እየከፈሉ ሥራ ላይ እንዲቆዩ መደረጉን አውስተዋል፡፡

በምርመራ ላይ ያሉትን ሆቴሎችንም ሆነ ፋብሪካዎችን ቀጣይ ዕድል ለማወቅ፣ ፍትሕ ሚኒስቴር ጉዳዩን ከመረመረ በኋላ ወደ ፍርድ ቤት በመውሰድ ውሳኔ ያሰጥባቸዋል ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የታሸጉና የተዘጉ ሆቴሎች በዋነኝነት ገንዘብ በማሸሽ፣ ጦርነቱን ከሕወሓት ጎን በመሆን በፋይናንስ በማገዝ በሕገወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ማስረጃ የተገኘባቸው መሆኑንና ጉዳያቸውም ክትትል እየተደረገበት መሆኑን ሚኒስተር ዴኤታው አስታውቀዋል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ

@tikvahethiopia

Report Page