DW

DW

ቲክቫህ ኢትዮጵያ

ዛሬ ሀዋሳ ያስቻለው የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በአቶ ዳጋቶ ኩምቤ መዝገብ የተካተቱ የ20 ተጠርጣሪዎችን ጉዳይ በመመልከት ትዕዛዝ ሰጠ።በዛሬው ቀጠሮ የተጠርጣሪዎቹ ደንበኞች ነን ካሉት ሶስት ጠበቆች በስተቀር  ከተጠርጣሪዎቹ አንዳቸውም በችሎቱ አልተገኙም።

ፍርድ ቤቱ «ተጠርጣሪዎች በችሎት ሳይገኙ ጉዳያቸውን በውክልና መከታተል የሚችሉት በፍትሃብሄር አንጂ፣ በወንጀል ክስ ይህ እንደማይቻል አስታውቋል።በመዝገቡ ከተካተቱት ሃያ ተጠርጣሪዎች መካከል አስራሁለቱ የፍርድ ቤት መጥሪያ እንደደረሳቸው ቀሪዎቹ ስምንቱ ግን እንዳልደረሳቸው ጠበቆቹ ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል። 

ከተጠርጣሪዎቹ ገሚሱ በወላይታ ሶዶ በአስር ላይ ሳሉ ባጋጠማቸው የአያያዝ ችግር ለከፍተኛ የስነ ልቦ ጉዳት እና ለህመም በመዳረጋቸው ፣ 11ኛዉ ተጠርጣሪ ደግሞ ከኮረና ተህዋሲ መስፋፋት ጋር ተያይዞ ባደረባቸው ስጋት  ሊቀርቡ እንዳልቻሉም ገልጸዋል። 

መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ ተጠርጣሪዎቹ በወላይታ ሶዶ የአስር ቆይታቸው ሰብአዊ መብታቸው መጠበቁን   አስታውቋል። «ቀደም ሲል ያላስመዘገቡትን ይህን ጉዳይ አሁን ማንሳታቸው ጉዳዩን ለማንዛዛት የተደረገ ነው ያለው መርማሪ ፖሊስ ሆስፒታል ሳይተኙ ችሎት ለመቅረብ አልቻልንም የሚለው ምክንያት አሳማኝ አይደለም >> ሲል ተቃውሟል።

ፍርድ ቤቱ በመጨረሻም << ተጠርጣሪዎች ለመጨረሻ ጊዜ በቀጣዩ ቀጠሮ ችሎት በመቅረብ አስከአሁን ያልቀረቡበትን ምክንያት አንዲያስረዱ ፣ በዛሬው ችሎት የቀረቡ ጠበቆችም በተጠርጣሪዎቹ የተወከሉ ስለመሆናቸው ለፍርድ ቤቱ አንዲያረጋግጡ እና የክርክር ሂደቱንም እንዲከታተሉ >> አዟል። 

በተጨማሪም በጠበቆች አማካኝነት የቀረቡት የህክምና ማስረጃዎች በአማረኛ ተተርጉመው እንዲቀርቡ ፣ መርማሪ ፖሊስም ቀደምሲል መጥሪያ ላልደረሳቸው ተጠርጣሪዎች አንዲደርሳቸው አንዲያደርግ በማዘዝ ጉዳዩን መስከረም 12 ቀን 2013 ዓም ለማየት ቀጠሮ መስጠቱን የሃዋሳው ወኪላችን ሸዋንግዛው ወጋየሁ ዘግቧል።

የወላይታ ዞን ከፍተኛ አመራሮች ባለፈው ነሀሴ 3፣2012 በፌዴሬሽኑ ውስጥ አዲስ የክልል መንግሥት ለመመስረት ያስችለናል ባሉት ረቂቅ ህገ መንግስት ዙሪያ በመወያየት ላይ እንዳሉ በጸጥታ ሀይሎች ቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ከዎላይታ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በተሰጣቸው የዋስት መብት ውሳኔ ከእስር መፈታታቸው የሚታወስ ነው ።

Report Page