DW

DW

ቲክቫህ ኢትዮጵያ

በኮንሶ ዞንና በአሌ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ ድንበሮች ላይ ዳግም ባገረሸ ግጭት ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ 12 ሰዎች ሞቱ ፣ 10 የሚሆኑ ቆሰሉ። ግጭቱ ዳግም የተቀሰቀሰው ባለፈው ቅዳሜና እሁድ የተደራጁ ያሏቸው ቡድኖች በአሌ ልዩ ወረዳ ወደሚገኙ መንደሮች ዘልቀው በመግባት ጉዳት ካደረሱ በኋላ መሆኑ ታዉቋል። 

ቡድኖቹ በአሌ ልዩ ወረዳ ገርጋማ እና ጉሮዜ በተባሉ ቀበሌያት ውስጥ በሚገኙ ሦስት መንደሮች ላይ አደረሱት በተባለው ጥቃት ከሞቱት በተጨማሪ አንድ የአምነት ተቋምን ጨምሮ በርካታ መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን የዓይን አማኖችና የልዩ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሳውራ ገበየሁ ለዶቼ ቬለ ( DW ) ተናግረዋል ።

በጉዳዩ ላይ ወደ ኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪም ሆነ የዞኑ ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ሃላፊዎች ተደጋጋሚ የስልክ ሙከራዎች ቢደረጉም ዋና አስተዳዳሪው ስብሰባ ላይ በመሆናቸው መምሪያ ሃላፊው ደግሞ ስልክ ባለማንሳታቸው አስተያየታቸውን ማካተት አልተቻለም። የአሌ ልዩ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ሃላፊው አቶ ሳውራ ገበየሁ ግን አሁን የሚታየው  ግጭት መፍትሄ ሊያገኘ ያልቻለው የደቡብ ክልል መንግስት ለችግሩ ትኩረት ሰጥቶ ድጋፍ ባለማድረጉ ነው ሲሊ ወቅሰዋል ። 

ግጭቱ መከሰቱን ለዶቼ ቬለ ( DW ) ያረጋገጡት የደቡብ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ምክትል ሃላፊ አቶ ታደሰ ዋጄቦ በክልሉ መንግስት በኩል የጉዳቱን መጠን የማጣራቱ ስራ በሂደት ላይ ቢገኝም አስከአሁን ግን ስድስት ሰዎች ስለመሞታቸው መረጃ እንዳላቸው ገልጸዋል። 

በኮንሶ ዞንና በአሌ ልዩ ወረዳ አዋሳኝ ድንበሮች ከባለፈው ወር መግቢያ አንስቶ በመሬት ይገባኛል ጥያቄ በተቀሰቀሰ ግጭት እስከአሁን ከሰላሳ የሚበልጡ ሰዎች ሲሞቱ ከሃያ ሺህ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸውን ዶቼ ቬለ  ዘግቧል።

Report Page