DW

DW

Greatful-Ethiopia

የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ከትናንት ጀምሮ ሲያካሂድ የነበረውን ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ አጠናቀቀ!

የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍቃዱ ተሰማ በሰጡት መግለጫ ፓርቲው በወቅታዊ ሀገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ በመምከር አቅጣጫዎችን አስቀምጧል።

በስብሰባውም ህወሃት እና ኦነግ ሸኔ ከውጭ ሀይሎች ጋር በመተባበር የታላቁን የኢትዮጵይ ህዳሴ ግድብ ግንባታን እና በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ ለማደናቀፍ ከውጭ ከውጭ ሀይሎች ጋር ተባብረው እየሰሩ መሆኑን ተመልክቷል ነው ያሉት።

ይህንንም ፓርቲው እንደሚታገለው አቶ ፍቃዱ ገልፀዋል።

ከፍተኛ አመራሩ እና አባላቱ አቋም ይዞ መታገል ላይ ክፍተት እንዳለባቸው መገምገሙን ጠቅሰዋል።

ሌብነትም እንደ ችግር ተነስቶ አባላቱም ሆነ አመራሩ ተግባሩን እንዲታገሉ አቅጣጫ መቀመጡን ነው ያመለከቱት።

በአመራሩ ውጤት ማስመዝገብ ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት ላይ ክፍተት እንዳለ መታየቱን ያነሱት አቶ ፍቃዱ በተደረገው ግምገማ እርምጃ መወሰዱን አስታውቀዋል።



Report Page