#DW

#DW

ቲክቫህ ኢትዮጵያ

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በተቀሰቀሰ ግጭት የሰዎች ህይወት አለፈ

በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል ባምባሲ ወረዳ  ከትናንትበስቲያ  በሁለት ቀበሌዎች መካከል በመሬት ይገባኛል ተጀመረው  በተባለው አለመግባባት በተቀሰቀሰው ግጭት የሰዎች ህይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች አስታውቀዋል፡፡  ግጭት በወረዳው በሚገኙት መንበደር 47፣48፣መንደር 55 እና ሌሎችም ስፋራዎች ተስፋፍተው  የ10 ሰዎች ህይወት  ማለፉንም ተናግረዋል፡፡

የአሶሳ ዞን ፖሊስ መመሪያ ኃላፊ ኮማንደር ያዕደቆብ አልማሙን በስልክ ለዲዳቢሊው እንደተናገሩትም በአካባቢው በተፈጠረው ግጭት በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ደርሰዋል፡፡ የአስር ሰዎች ህይወት ማለፉንም ያረጋገጡ ሲሆን አስራ አራት  ሰዎች ደግሞ በወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስራ መዋላቸውን ገልጸዋል፡፡

ከአሶሳ ከተማ በ42 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚትገኘው ባምባሲ ወረዳ መንደር 48 እና ጀማጻ በተባሉ ቀበሌዎች መካከከል ለረዥም ጊዜ የቆየ የመሬት ይገባኛል ጥያቄ እንደነበር የአካቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ በዚሁ ስፋራ ከትናንት በስቲያ በመሬት ይገባኛል ጥያቄ በተፈጠረው አለመግባባት የተቆጡ ወጣቶች የተቃዉሞ ድምጽቸውን ማሰማት ሲጀምሩ የአካባቢው ፖሊስ ወደ ስፍራው በመሰማራት ለማረጋጋት ሲሞክር ግጭት ተከስቶ ወዲው የአራት ወጣቶች ህይወት ማለፉን ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የባምባሲ ወረዳ መንደር 47 ነዋሪዎች በስልክ ገልጸዋል፡፡

በመንደር 47 ብቻ ስምንት ሰዎች ላይ  የመቁሰል አደጋ መድረሱን አብራርተዋል፡፡ለግጭቱ መነሻ ነበር የተባለው መሬት ከባምባሲ ከተማ 9 ኪ.ሜ ርቀት ላይ  በመንደር 48 እና ጀማጺያ በተባሉ ቀበሌዎች መካከል የሚገኝና ከዚህ ቀደም ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ለ12 ሰዎች ተሰጥቶ እንደነበር የገለጹት የመንደር 48 ነዋሪ የሆኑት አቶ ጀማል አበዱልቃድር በበኩላቸው ከዚህ በኋላ ማረስ አትችሉም ተብለው ከቦታው መነሳታቸውንና ምትክ መሬት ይሰጣችኋል መባላቸውን ጠቁመዋል፡፡

ባለፈው ረቡዕ በጀመረው ግጭት ምክንያት  ሰዎች ወደ እርሻ ማሳቸው መሄድ አልቻሉም ብለዋል፡፡ በባምባሲ አራት ቀበሌዋች ውስጥ ለሁለት ቀናት ምንም ዓይነት የሰው እንቅስቃሴ እንዳልነበር የጠቆሙት አቶ ጀማል ትናንት ከሰዓት የመከላከያ ሰራዊት ወደ ገጠሩ አካባቢ ከተሰማራ በኃላ መጠነኛ እንቅሰቃሴ መጀመሩንም አክለዋል፡፡ በግጭቱ ጉዳት የደረባቸው ሰዎችም ቁጥር እጨመረ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በቤኒሻንል ጉሙዝ ክልል የአሶሳ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ያዕቆብ አልማሙን ሰሞኑንን በባምበሲ ወረዳ የገጠር ቀቤዎች ውስጥ ግጭት እንደነበር አረጋጠዋል፡፡ በተፈጠረውም ግጭት የአስር ሰዎች ህይወት ማለፉን እና ንብረትም መውደሙን አስረድተዋል፡፡

በስምንት ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ ጉዳት መድሩን ኮማንደር ያዕቆብ ተናግረዋል፡፡በወረዳው ከዚህ በፊት ምንም ዓይነት የጸጥታ ችግር  እንዳልነበር የገለጹት ኃላፊው  የፌደራል እና መከላከያ ሰራዊት አካባቢው እያረጋጉ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ በአካባቢው ሰላም ለማስፈን ያስችላል የተባሉ ውይይቶችንም ከሀገር ሽማግሌዎች፣ከሀይማኖት አባቶችና ከወጣቶች ጋር እየተደረጉ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

Report Page