DW

DW

ቲክቫህ ኢትዮጵያ

የሶማሌ ኢሳ ጎሳ ሽማግሌዎች አቤቱታ!

የሶማሌ ኢሳ ጎሳ ኡጋዛዊ ምክር ቤት ሽማግሌዎች ኮንትሮባንድን በመከላከል ሰበብ ሰላማዊ ዜጎች እየተገደሉ ነው ሲሉ ድርጊቱን ተቃውመዋል። ድርጊቱን ይፈፅማሉ ያሏቸው አካላት ለህግ እየቀረቡ ባለመሆኑ መንግስት አስፈላጊውን እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

የሶማሌ ሽማግሌዎች ስላቀረቡት አቤቱታ የተጠየቁት የድሬዳዋ አስተዳደር ባለሥልጣን ጉዳዩ እየተመረመረ መሆኑን ተናግረዋል  ኡጋዛዊ ምክር ቤቱን በመወከል መግለጫ ከሰጡት ሽማግሌዎች አንዱ የሆኑት አቶ መሀመድ አዎሙሴ ጌሌ ኮንትሮባንድ ለመከላከል በሚል ሰበብ የሚጠፋው የሰው ህይወት ያሳስበናል ብለዋል።

አቶ አሰዌ ፋራህ በበኩላቸው በቅርቡ በድሬደዋ ኮንትሮባንድን ለመከላከል በሚል በፀጥታ ኃይሉ በተወሰደ ርምጃ የሞተው ወጣትም ሆነ የቆሰሉት ከኮንትሮባንድ ጋር ግንኙነት የሌላቸው መሆኑን በመጥቀስ ዓላማው ሌላ መሆኑን ተናግረዋል። መሰል ድርጊት በተለያዩ ጊዜያት ተፈፅሟል የሚሉት አቶ መሀመድ ተመሳሳይ ድርጊት ሊፈፀም እንደማይገባ ጠቅሰው ድርጊቱን የሚፈፅሙ አካላትም በህግ መጠየቅ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በምክር ቤቱ ሽማግሌዎች ስለቀረበው አቤቱታ ዶቼቬለ ያነጋገራቸው በፌደራል ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ የድሬደዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ምህረቱ ቁምላቸው በወቅቱ ኮንትሮባንድን ለመቆጣጠር ከተወሰደ ርምጃ ጋር የተፈጠሩ ጉዳዮች ላይ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን አስረድተዋል ። አቶ ምህረቱ ምርመራው እንደተጠናቀቀ ክስ እንደሚመሰረት መዝገቡ ወደሚመለተው አካል ይላካል ብለዋል።

Report Page