designing

designing

ቲክቫህ ኢትዮጲያ

ሲሼልሳዊቷ ስራ ፈጣሪ ከሙዝና ዘንባባ የተለያዩ አልባሳትን ሰራች

እርሶ ልብሶችን ለመግዛት  ወደ ገበያ አቅንተው አልያም  የልብስ ስጦታ ከወዳጆ ቢቀርብልዎ ይሄ ልብስ እንደሙዝ ካለ ፍራፍሬ ወይም አትክልት  ነው የተሰራው ቢባሉ ያምኑ ይሆን ?ሲሼልሳዊቷ የስራ ፈጣሪ ማሪዬት ዳይን ግን ይህንን እውን አድርጋዋለች፡፡ ከሙዝ፣ ከዘንባባ እንዲሁም አናናስ ከሚገኝ ቃጫ ልብሶችን መስራት ችላለች፡፡

ዳይን ይህን ህልሟን ልታሳካ የቻለችው ቶኒዪ ኤሉማሉ ከተባለ ፋውንዴሽን ባገኘችው የአመስት ሺ ዶላር ድጋፍ ነው፡፡ በፋውንዴሽኑ ባለፈው አመት ከተመረጡ 1ሺ አፍሪካውያን መካከል እሷና የአገሯ ልጅ ሞንያ ፍሎረንቲን ሲሼልስን ወክለው የእድሉ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ 

ዳይን “እኔ እንደ አንድ ሞዴል እና ወጣት አፍሪካዊ ሴት ዘርፉ ላይ እንዴት ተጽህኖ መፍጠር እንዳለብኝ አውቃለሁ፣ ለዛም ነው አገር በቀል የሆኑ የስራ ፈጠራ መንገዶችን ተጠቅሜ ይሄንን ልሰራ የቻልኩት” ስትል ሀሳቧን ሰንዝራለች፡፡

አልባሳቱን በቀላል ዘዴ እንደቢላ ባሉ የቤት ውስጥ መገልገያዎች ብሎም ውሃን በመጠቀም በእግሮቿ ይዛ በመላጥ የምትሰራ ሲሆን ስራው ግን ከፍተኛ ድካም እንዳለውና ትዕግስት እንደሚጠይቅ  ትገልጻለች፡፡ ልብሶቹ የሚሰሩበትን ቃጫ ለማውጣት ደግሞ ለረጅም ሰዓት  እሳትን በመጠቀም ሳትሰለች እንደምትሰራም ዳይን አስረድታለች፡፡

የተዘጋጁትን ቃጫዎች ወደ ቀጭን ክሮች በመለወጥ ልብስ መሸመኛ ውስጥ አስገብታ በምትፈልገው ዲዛይን ልብሶቹን አንደምታዘጋጅ ተናግራለች፡፡

ከሙዝ ዘንባባና አናናስ ከመሳሰሉት ዕጽዋት የሚሰሩትን ልብሶች ለመሸጥ የኦንላይን ግብይት እንደምትጠቀም የምትናገረው  ስራ ፈጣሪዋ፣  የኦን ላይን ግብይቱ እቀዎችን ከመሸጥ ባለፈ ለእርስ በእርስ ግንኙነትና እንደሷ ካሉ ስራ ፈጣዎች ጋር መወያያ መድረክም ሆኗታል፡፡

በአሁኑ ወቅት የፋሽን ኢንዱስትሪው ከፍተኛ ገቢ እያስገኘ በመምጣቱ  ሲሼልስም የዚሁ አካል በመሆን በዘርፉ ላይ ተሳትፎዋ ይጠነክራል ማለቷም ተዘግቧል፡፡

ማሪዬት ዳይን ከስራ ፈጣሪነቷ በተጨማሪ ሞዴልና የአሻንጉሊት አምራች ድርጅት ባለቤት ናት ሲል ያስነበበው ኦል አፍሪካን ድረ ገጽ ነው፡፡

Report Page