Decision

Decision

@AKHC TEENAGERS

ብዙ ጊዜ አንድን ነገር ለማድረግ ወይም ላለማድረግ ለራሳችን ቃል እንገባለን...."ከዚህ ቦሀላ"  "ሁለተኛ እንደዚህ አላደርግም"  "እኔ ሞቼያለው ይህን ባላደርግ"....እንደነዚህ አይነት ቃላቶችን ካንዴም ሁለቴ ለተለያየ አይነት ምክንያት አብዛኞቻችን ተጠቅመናቸዋል ከዛም ለጥቂት ጊዜ እንዳልነው እንሆንና ከዛ እነዚያ ውሳኔዎች ፈፅመው ከአዕምሮአችን ይጠፋሉ፡፡ ምክንያቱም አብዛኞቻችን መሆን ስለምንፈልገው እናወራለን እንጂ የወሰነውን ለመሆን የሚጠይቁትን ዋጋ አንከፍልም፡፡ ለውጥ የረዥም ጊዜ ውጤት ቢሆንም ወሳኔ ግን የአንድ ጊዜ ነው፡፡ ውሳኔ እንደ ዘር ነው በውስጡ ያለውን ፍሬ ማውጣት የሚችለው በተንከባከብነው ልክ ነው፡፡ ውሳኔ ወደ ለውጥ የሚያድገው በእየቀኑ እለወጣለው እያሉ በማወራት ወይም ለውጡን በመመኘት ብቻ ሳይሆን ውሳኔያችንን ለመሆን በመስራት ነው ለውጥ ያለው፡፡ ለምሳሌ አንድ ገበሬ የዘራውን መንከባከብ ትቶ በዝናቡም በደረቁም ወር ዝም ብሎ ጠዋት እየተነሳ ዘርን በመዝራት ጊዜውን ቢያሳልፍ ምን ይባላል? ሁሉም ሰው የሚለው ጤና የለውም ብሎ ያስባል፡፡ ተግባር የሌለው ውሳኔም እንዲሁ ነው፡፡ መሆን የምትፈልጉትን ብዙ በማወራት ሳይሆን ብዙ በመስራት መሆን ይቻላል፡፡

Report Page