#D

#D


ደቡብ ክልል❓

በደቡብ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የተከሰተው ችግር ምክንያቱ ፖለቲካዊና የአመራር ስርዓቱ አለመጠናከር መሆኑን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ገለፁ። የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ለማስከበር የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት በሚያከናውናቸው ተግባራት ላይ ከዞን እስከ ወረዳ ካሉ የሰላምና ጸጥታ አመራሮች ጋር ትላንይ በሃዋሳ ከተማ ተወያይተዋል። በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኤልያስ ሽኩር እንዳሉት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በክልሉ ውስጥ ሀገራዊ መልክ ያላቸው የተለያዩ ችግሮች እየተከሰቱ ነው።

ለእዚህም ካለፉት ስድስትና ሰባት ወራት ወዲህ በክልሉ ከፍተኛ የጸጥታ ስጋት እየገጠመ መሆኑን ጠቁመው በዚህም ምክንያት የክልሉ ህዝቦች ከፍተኛ ስጋት ውስጥ መግባታቸውን ተናግረዋል። በአንዳንድ አካባቢዎች በሰላም ወጥቶ መግባትና ያፈሩትን ሀብትና ንብረት ባልተጠበቀ ጊዜ መውደም አልፎ አልፎ እየገጠመ መሆኑንም ገልጸዋል። እንደየአካባቢው ሁኔታ ቢለያይም በአንዳንድ አካባቢዎች አሁንም የስጋት ምልክቶች እየታዩና እየሰፉ የሚሄዱ የሚመስሉ ችግሮች እየታዩ መሆናቸውን ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል። በእዚህም የክልሉ የጸጥታ ስራ በጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት እንዲመራ ተወስኖ ወደ ሥራ መገባቱን አቶ ኤሊያስ ጠቁመዋል። “የችግሩ መንስኤ ፖለቲካዊ በመሆኑ መፍትሄውም ፖለቲካዊ ነው ሲሉ” ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ገልጸዋል። 

🏷ከክልሉ 18 ዞኖችና ስምንት ልዩ ወረዳዎች የተውጣጡ የሰላምና የጸጥታ መምሪያና ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ከመከላከያና ፌዴራል ፖሊስ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ከክልሉ ልዩ ኃይልና ፖሊስ ጋር በኮማንድ ፖስቱ ተግባራት ላይ በመወያየት አቅጣጫና መመሪያ ያወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

 

Via #ENA

@tsegabwolde @tikvahethiopia

Report Page